አስፈላጊ በሆነ የሕክምና ዘዴ ላይ ያተኮረ የቪዲዮ ፊልም
የሕግ ባለሞያዎችም ሆኑ በሕክምናው ዘርፍ የተሰማሩ ሰዎች ለታካሚዎቻቸው መብትና ለሚከተሉት የሥነ ምግባር ደንብ የበለጠ ትኩረት መስጠት ጀምረዋል። ይህም አዳዲስ የሕክምና መንገዶችና ዘዴዎች ብቅ እንዲሉ ያደረገ ሲሆን የይሖዋ ምሥክሮችም ከዚህ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ። (ሥራ 15:28, 29) በደም ምትክ የሚሰጥ ሕክምና—የሕሙማንን መብትና ፍላጎት ማክበር የተሰኘው የቪዲዮ ፊልም በዚህ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ነው። ይህንን የቪዲዮ ፊልም ከተመለከታችሁት በኋላ የተማራችሁትን ለመከለስ በሚቀጥሉት ጥያቄዎች መጠቀም ትችላላችሁ።—ማሳሰቢያ:- ፊልሙ አልፎ አልፎ ቀዶ ሕክምና ሲከናወን የሚያሳይ በመሆኑ ወላጆች ከትናንሽ ልጆቻቸው ጋር ፊልሙን ሲመለከቱ አስተዋዮች መሆን ይኖርባቸዋል።
(1) በሕክምናው መስክ የተሰማሩ አንዳንድ ሰዎች ደም በመስጠት የሚደረግ ሕክምናን እንደገና ማጤን የጀመሩት ለምንድን ነው? (2) ያለ ደም ሊከናወኑ ከሚችሉ ከባድ ቀዶ ሕክምናዎች ውስጥ ሦስት ምሳሌዎች ጥቀስ። (3) በዓለም ዙሪያ ሕመምተኞቻቸውን ያለ ደም ለማከም ፈቃደኛ መሆናቸውን የገለጹ ምን ያህል ሐኪሞችና የቀዶ ሕክምና ባለሞያዎች ይገኛሉ? እንዲህ ለማድረግ ፈቃደኞች የሆኑትስ ለምንድን ነው? (4) በቅርቡ በሆስፒታሎች ውስጥ በተካሄዱ ጥናቶች መሠረት ደም መውሰድን በተመለከተ ምን ነገር ሊታወቅ ችሏል? (5) ደም ከመውሰድ ጋር በተያያዘ ምን ዓይነት የጤና እክሎች ሊያጋጥሙ ይችላሉ? (6) በርካታ ባለሞያዎች በደም ምትክ የሚሰጡ የሕክምና አማራጮች የሚያስገኟቸውን ጥቅሞች በተመለከተ ምን መደምደሚያ ላይ ደርሰዋል? (7) ደም ማነስ ከምን ይመጣል? ሰዎች ለአደጋ ሳይጋለጡ የደማቸው መጠን ምን ያህል ዝቅ ሊል ይችላል? ሁኔታውን ለማስተካከል ምን ማድረግ ይቻላል? (8) የአንድ ሕመምተኛ ሰውነት ተጨማሪ ቀይ የደም ሕዋስ እንዲያመርት ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው? (9) ሐኪሞች በቀዶ ሕክምና ወቅት የሚፈስሰውን ደም ለመቀነስ በየትኞቹ መንገዶች ይጠቀማሉ? (10) በደም ምትክ የሚሰጡ ሕክምናዎች ለትናንሽ ልጆች ወይም ለሕይወት የሚያሰጋ ድንገተኛ አደጋ ላጋጠማቸው ሰዎች ውጤታማ ሊሆኑ ይችላሉ? (11) ከጥሩ ሕክምና ተቀዳሚ የሥነ ምግባር መመሪያዎች አንዱ ምንድን ነው? (12) ክርስቲያኖች በደም ምትክ ከሚሰጡ የሕክምና አማራጮች ውስጥ የሚቀበሉትን አስቀድመው መወሰናቸው አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ይህንን ማድረግ የምንችለውስ እንዴት ነው?
በፊልሙ ላይ የቀረቡ አንዳንድ የሕክምና አማራጮችን መቀበል እያንዳንዱ ሰው በመጽሐፍ ቅዱስ በሠለጠነ ሕሊናው ተጠቅሞ የሚያደርገው የግል ውሳኔ ነው። እናንተም ሆናችሁ ልጆቻችሁ የትኛውን በደም ምትክ የሚሰጥ ሕክምና እንደምትቀበሉ ወስናችኋል? የይሖዋ ምሥክር ላልሆኑ የቤተሰባችሁ አባላትም ስለ ውሳኔያችሁና ለምን እንደዚህ ዓይነት ውሳኔ እንዳደረጋችሁ በዝርዝር ልትነግሯቸው ይገባል።—በሰኔ 15, 2004 እና በጥቅምት 15, 2000 የመጠበቂያ ግንብ እትሞች ላይ የወጡትን “የአንባቢያን ጥያቄዎች” ተመልከት።