የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 1/10 ገጽ 3
  • ዛሬ ነገ እያልክ ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ዛሬ ነገ እያልክ ነው?
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2010
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ዛሬ ነገ እያልክ ነው?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
  • ድንገት ሊያጋጥም ለሚችል የጤና ችግር ተዘጋጅተሃል?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2012
  • ምን አማራጮች እንዳሉህ ታውቃለህ?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2009
  • ምን አማራጮች እንዳሉህ ታውቃለህ?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2011
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2010
km 1/10 ገጽ 3

ዛሬ ነገ እያልክ ነው?

ምኑን? ብለህ ትጠይቅ ይሆናል። ለተጠመቁ የይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን የሕክምና መመሪያ ካርድ መሙላቱን። ‘ነገ የሚሆነውን ስለማታውቅ’ ድንገተኛ ሁኔታ አጋጥሞህ ሐኪም ቤት ብትገባ ምን ዓይነት ሕክምናዎችን እንደምትፈልግ አስቀድመህ መወሰንህና ይህን ውሳኔህን በጽሑፍ ማስፈርህ እጅግ አንገብጋቢ ጉዳይ ነው። (ያዕ. 4:14፤ ሥራ 15:28, 29) በደም ምትክ የሚሰጥ ሕክምና—የሕሙማንን መብትና ፍላጎት ማክበር የተባለው ቪዲዮ የተዘጋጀው በዚህ ረገድ አንተን ለመርዳት ታስቦ ነው። ይህን ቪዲዮ ከተመለከትክ በኋላ ከዚህ በታች በቀረቡት ጥያቄዎች አማካኝነት ትምህርቱን በመከለስ ሁኔታውን በጸሎት አስብበት።—ማሳሰቢያ፦ ቪዲዮው ቀዶ ሕክምና ሲደረግ የሚያሳዩ ክፍሎች ስላሉት ወላጆች ከትናንሽ ልጆቻቸው ጋር ፊልሙን ሊያዩት ይገባ እንደሆነና እንዳልሆነ አመዛዝነው መወሰን ይኖርባቸዋል።

(1) በሕክምናው መስክ የተሰማሩ አንዳንድ ባለሙያዎች ደም በመስጠት የሚደረግ ሕክምናን እንደገና ማጤን የጀመሩት ለምንድን ነው? (2) ያለ ደም ከተከናወኑ ከባድ ቀዶ ሕክምናዎች ውስጥ ሦስት ምሳሌዎች ጥቀስ። (3) በዓለም ዙሪያ ሕሙማንን ያለ ደም ለማከም ፈቃደኛ መሆናቸውን የገለጹ ምን ያህል ሐኪሞችና የቀዶ ሕክምና ባለሞያዎች ይገኛሉ? እንዲህ ለማድረግ ፈቃደኞች የሆኑትስ ለምንድን ነው? (4) በቅርቡ በሆስፒታሎች ውስጥ በተካሄዱ ጥናቶች መሠረት ደም መውሰድን በተመለከተ ምን ነገር ሊታወቅ ችሏል? (5) ደም ከመውሰድ ጋር በተያያዘ ምን ዓይነት የጤና እክሎች ሊያጋጥሙ ይችላሉ? (6) በርካታ ባለሙያዎች በደም ምትክ የሚሰጡ የሕክምና አማራጮች የሚያስገኟቸውን ጥቅሞች በተመለከተ ምን መደምደሚያ ላይ ደርሰዋል? (7) ደም ማነስ ከምን ይመጣል? ሰዎች ለአደጋ ሳይጋለጡ የደማቸው መጠን ምን ያህል ዝቅ ሊል ይችላል? ሁኔታውን ለማስተካከል ምን ማድረግ ይቻላል? (8) የአንድ ሕመምተኛ ሰውነት ተጨማሪ ቀይ የደም ሕዋስ እንዲያመርት ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው? (9) ሐኪሞች በቀዶ ሕክምና ወቅት የሚፈስሰውን ደም ለመቀነስ በየትኞቹ መንገዶች ይጠቀማሉ? (10) በደም ምትክ የሚሰጡ ሕክምናዎች ለትናንሽ ልጆች ወይም ለሕይወት የሚያሰጋ ድንገተኛ አደጋ ላጋጠማቸው ሰዎች ውጤታማ ሊሆኑ ይችላሉ? (11) ከጥሩ ሕክምና ተቀዳሚ የሥነ ምግባር መመሪያዎች አንዱ ምንድን ነው? (12) ክርስቲያኖች በደም ምትክ ከሚሰጡ የሕክምና አማራጮች ውስጥ የሚቀበሉትን አስቀድመው መወሰናቸው አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ይህንን ማድረግ የምንችለውስ እንዴት ነው?

በፊልሙ ላይ የቀረቡ አንዳንድ የሕክምና አማራጮችን መቀበል እያንዳንዱ ሰው በመጽሐፍ ቅዱስ በሠለጠነ ሕሊናው ተጠቅሞ የሚያደርገው የግል ውሳኔ ነው። እናንተም ሆናችሁ ልጆቻችሁ ምን ዓይነት ሕክምና እንደምትፈልጉ አስቀድማችሁ ወስናችኋል? ውሳኔያችሁን በሕክምና መመሪያ ካርድ ላይ አስፍራችኋል? በዚህ ጉዳይ ላይ ይበልጥ የተሟላ መረጃ ለማግኘት “ከአምላክ ፍቅር አትውጡ” ከተባለው መጽሐፍ ላይ ምዕራፍ 7ን እና በምዕራፉ ውስጥ የተጠቀሱትን ተጨማሪ ጽሑፎች ወይም ክፍሎች በጥንቃቄ ከልሱ። በተጨማሪም “የደም ክፍልፋዮችንና የራሴን ደም በመጠቀም የሚሰጡ ሕክምናዎችን በተመለከተ ምን ውሳኔ ማድረግ ይኖርብኛል?” የሚለውን በኅዳር 2006 የመንግሥት አገልግሎታችን እትም ላይ የወጣውን አባሪ ተመልከቱ። በመጨረሻም ያደረጋችሁትን ውሳኔ በሕክምና መመሪያ ካርዳችሁ ላይ በትክክል ማስቀመጣችሁን አረጋግጡ። የአደጋ ጊዜ ተጠሪዎች እንዲሆኑ የመረጣችኋቸው ሰዎችና የይሖዋ ምሥክር ያልሆኑ የቤተሰባችሁ አባላት ያደረጋችሁትን ውሳኔ በሚገባ እንዲያውቁት ማድረግ ይኖርባችኋል።

[በገጽ 3 ላይ የሚገኝ ሣጥን]

• እናንተም ሆናችሁ ልጆቻችሁ ምን ዓይነት ሕክምና እንደምትፈልጉ አስቀድማችሁ ወስናችኋል?

• ድንገተኛ ሁኔታ ቢያጋጥማችሁ በደንብ የተሞላ የሕክምና መመሪያ ካርድ ይዛችኋል?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ