ጥር 25 የሚጀምር ሳምንት
ጥር 25 የሚጀምር ሳምንት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መሳፍንት 5-7
ቁ. 1፦ መሳፍንት 7:1-11
ቁ. 2፦ በራእይ 17:1 ላይ የተገለጸችውን ‘ታላቂቱ ጋለሞታ’ ለይተን ማወቅ የምንችለው እንዴት ነው?
ቁ. 3፦ አንድ ሰው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተገለጸው ሲኦል መውጣት ይችላል? (rs ገጽ 171 አን. 1-3)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ፦ በየካቲት ወር የምናበረክተው ጽሑፍ። በዚህ ወር የሚበረከተው ጽሑፍ ያሉትን ጠቃሚ ገጽታዎች በአጭሩ ግለጽ። አንድ አስፋፊ መደበኛ ባልሆነ መንገድ በሚመሠክርበት ወቅት በዚህ ጽሑፍ ተጠቅሞ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ሲያስጀምር የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
20 ደቂቃ፦ “ዛሬ ነገ እያልክ ነው?” በጉባኤ ሽማግሌ በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። አንድ አስፋፊ የሕክምና መመሪያ ካርድ ዓላማ ምን እንደሆነ ለሐኪሙ ሲያስረዳና በግል ፋይሉ ውስጥ እንዲቀመጥለት ሲጠይቅ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ሐኪሙ በፋይል ውስጥ እንደሚያስቀምጥለት ለወንድም ቃል ይገባለታል። የመጨረሻውን አንቀጽ አንብበህ ክፍሉን ደምድም።