የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 4/05 ገጽ 1
  • በስብከቱ ሥራ ጽኑ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በስብከቱ ሥራ ጽኑ
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2005
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መስበካችሁን ቀጥሉ!
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
  • “ሂዱና ከሁሉም ብሔራት ሰዎችን ደቀ መዛሙርት አድርጉ”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016
  • “የይሖዋን ስም አወድሱ”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2024
  • ማዘናጊያዎችን በማስወገድ ነቅተን እየኖርን ነውን?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2005
km 4/05 ገጽ 1

በስብከቱ ሥራ ጽኑ

1 ዘመኑ አስጨናቂ ነው፤ የእርስ በርስ ጦርነት፣ የጎሣ ግጭት፣ የተፈጥሮ አደጋዎች እንዲሁም ሌሎች የጭካኔ ድርጊቶች በዓለም ላይ የተለመዱ ነገሮች ሆነዋል። ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ በአሁኑ ወቅት የሰው ዘር ምሥራች ያስፈልገዋል። ሆኖም ለመንፈሳዊ ነገሮች ቸልተኛ መሆን በስፋት ይታያል። በአንዳንድ አካባቢዎች ሰዎችን እቤታቸው ማግኘት አስቸጋሪ ከመሆኑም በላይ ለመልእክታችን ጆሮ የሚሰጥ ወይም መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት የሚፈልግ ሰው ማግኘት አዳጋች ሊሆን ይችላል። ያም ሆኖ ስለ ተቋቋመው የአምላክ መንግሥት የሚናገረውን ምሥራች በጽናት መስበካችን በጣም አስፈላጊ ነው።—ማቴ. 24:14

2 ለሰዎች ያለው ፍቅር:- የስብከት ሥራችን ይሖዋ ለሰው ልጆች ፍቅር እንዳለው በጉልህ ያሳያል። ይሖዋ ‘ሁሉ ለንስሐ እንዲበቃ’ እንጂ ‘ማንም እንዲጠፋ’ አይፈልግም። (2 ጴጥ. 3:9፤ ሕዝ. 33:11) በመሆኑም ኢየሱስ እንደተናገረው አምላክ “አስቀድሞ . . . ወንጌል ለሕዝብ ሁሉ መሰበክ አለበት” ሲል አውጇል። (ማር. 13:10) አምላክ ሰዎች ወደ እሱ በመመለስ በሰይጣን ዓለም ላይ ከሚመጣው የቅጣት ፍርድ እንዲተርፉ ግብዣ እያቀረበ ነው። (ኢዩ. 2:28, 29, 32፤ ሶፎ. 2:2, 3) ይሖዋ እንዲህ ዓይነቱን አጋጣሚ እንድናገኝ በማድረጉ አመስጋኞች ልንሆን አይገባንም?—1 ጢሞ. 1:12, 13

3 የ2004 የአገልግሎት ዓመት ዓለም አቀፍ ሪፖርት እንደሚያሳየው በየወሩ በአማካይ 6,085,387 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ተመርተዋል፤ እንዲሁም በእያንዳንዱ ሳምንት በአማካይ 5,000 የሚያህሉ ሰዎች አዳዲስ ደቀ መዛሙርት በመሆን ተጠምቀዋል! ራሳቸውን ከወሰኑት ከእነዚህ ደቀ መዛሙርት መካከል አንዳንዶቹ የተገኙት አስፋፊዎች በአገልግሎት ክልላቸው ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች ሁሉ በጽናት ለመስበክ ያደረጉትን ጥረት ይሖዋ ስለባረከላቸው ነው። ይህ ውጤት በጉባኤ ውስጥ ታላቅ ደስታ አስገኝቷል፤ በዚህ ሕይወት አድን ሥራ ላይ ከይሖዋ ጎን መሰለፍ መቻል እንዴት ያለ ግሩም መብት ነው!—1 ቆሮ. 3:5, 6, 9

4 የአምላክን ስም ማወደስ:- በጽናት የምንሰብከው ይሖዋን በሕዝብ ፊት ለማወደስና በሁሉም ሰው ፊት ስሙ እንዲቀደስ ለማድረግ ነው። (ዕብ. 13:15) ሰይጣን፣ አምላክ የሰው ልጆችን ችግር ለማስወገድ የሚያስችል ኃይል የለውም፣ ለሚደርስባቸው መከራ ግድ አይሰጠውም ወይም ደግሞ ጨርሶ የለም ብለው እንዲያምኑ በማድረግ “ዓለምን ሁሉ” በማሳት ላይ ይገኛል። (ራእይ 12:9) በስብከት ሥራችን አማካኝነት ድንቅ ስለሆነው የሰማዩ አባታችን ለሚናገረው እውነት ጥብቅና እንቆማለን። ስሙን አሁንም ሆነ ለዘላለም ማወደሳችንን እንቀጥል።—መዝ. 145:1, 2

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ