የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 5/07 ገጽ 3
  • የጥያቄ ሣጥን

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የጥያቄ ሣጥን
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2007
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በአክብሮት ተጋብዘሃል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ መመሪያ
    የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ መመሪያ
  • ስብሰባዎችን በሰዓቱ ጀምራችሁ በሰዓቱ ጨርሱ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
  • አዲስ የጉባኤ ስብሰባ ፕሮግራም
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2007
km 5/07 ገጽ 3

የጥያቄ ሣጥን

◼ የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤትን፣ የአገልግሎት ስብሰባን፣ የሕዝብ ስብሰባንና የመጠበቂያ ግንብ ጥናትን የመክፈቻ መዝሙር ማስተዋወቅ የሚቻለው እንዴት ነው? ማስተዋወቅ የሚኖርበትስ ማን ነው?

በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ የሚዘመረው የእያንዳንዱ ሳምንት የመክፈቻ መዝሙር በጥቅምት የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ላይ በሚወጣው የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ፕሮግራም ላይ ይዘረዘራል። በእያንዳንዱ ሳምንት በአገልግሎት ስብሰባ ላይ የሚዘመሩት የመክፈቻና የመደምደሚያ መዝሙሮች በመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 2 ላይ ይወጣሉ። በተመሳሳይ በሳምንታዊው የመጠበቂያ ግንብ ጥናት ላይ የሚዘመሩት መዝሙሮች በእያንዳንዱ መጠበቂያ ግንብ እትም ገጽ 2 ላይ ይገኛሉ። ለእያንዳንዱ ስብሰባ የተመደቡት መዝሙሮች የዚያ ስብሰባ ክፍል ስለሆኑ መዝሙሮቹን ማስተዋወቅ የሚኖርበት ቀደም ሲል የተደረገው ስብሰባ ሊቀ መንበር ሳይሆን ቀጣዩን ስብሰባ የሚመራው ወንድም ነው።

ለምሳሌ የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት የበላይ ተመልካች ለአድማጮች ሰላምታ ካቀረበና የመክፈቻውን መዝሙር ካስተዋወቀ በኋላ ትምህርት ቤቱን ይመራል። ከዚያም በአገልግሎት ስብሰባ ላይ የመጀመሪያውን ክፍል የሚያቀርበውን ወንድም ወደ መድረክ ይጋብዛል። የአገልግሎት ስብሰባውን የመክፈቻ መዝሙር ማስተዋወቅ የሚኖርበት ይህ ወንድም ነው።

በተመሳሳይም የሕዝብ ስብሰባን የሚያስተዋውቅ ሊቀ መንበር ይኖራል። ሊቀ መንበሩ ለተሰብሳቢዎቹ ሞቅ ያለ ሰላምታ ካቀረበ በኋላ በተናጋሪው የተመረጠውን የመክፈቻ መዝሙር እንዲዘምሩ ይጋብዛል። ከዚያም እርሱ ራሱ (ወይም ቀደም ሲል የተመደበ ብቃት ያለው ሌላ ወንድም) ስብሰባውን በጸሎት ይከፍታል። ሊቀ መንበሩ ተናጋሪውንና የንግግሩን ርዕስ ያስተዋውቃል። ንግግሩ ካለቀ በኋላ ሊቀ መንበሩ ተናጋሪው የጠቀሳቸውን ነጥቦች እንደገና ሳይጠቅስ ለቀረበው ትምህርት አጭር ምስጋና ያቀርባል። የቀጣዩን ሳምንት የሕዝብ ንግግር ርዕስ ያስተዋውቅና ሁሉንም ተሰብሳቢዎች እዚያው ቆይተው ቀጥሎ በሚደረገው የመጠበቂያ ግንብ ጥናት እንዲካፈሉ ይጋብዛል። ሊቀ መንበሩ አድማጮች ተናጋሪው ለመጣበት ጉባኤ ፍቅራዊ ሰላምታቸውን መላክ ይፈልጉ እንደሆነ መጠየቅ አያስፈልገውም። ከዚያም ሊቀ መንበሩ የመጠበቂያ ግንብ ጥናት መሪውን ወደ መድረክ ይጋብዛል።

የመጠበቂያ ግንብ ጥናቱን የሚመራው ወንድም ለጥናቱ የተመደበውን የመጀመሪያ መዝሙር ያስተዋውቃል። ከዚያም ጥናቱን ከዚህ ቀደም በጽሑፎች ላይ በወጣው መመሪያ መሠረት ከመራ በኋላ የመደምደሚያውን መዝሙር ያስተዋውቃል። ብዙ ጊዜ እንደሚደረገው የመጠበቂያ ግንብ ጥናት መሪው የመደምደሚያውን ጸሎት እንዲያቀርብ የሕዝብ ንግግሩን ያቀረበውን ወንድም ይጋብዛል።

እነዚህን መመሪያዎች ተግባራዊ ማድረጋችን የጉባኤ ስብሰባዎቻችንን ወጥነት ባለው መንገድ ለመምራት ያስችላል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ