ወደኋላ አትበሉ!
1. “መልካም ነገር ከማድረግ” ወደኋላ ማለት እንደማንፈልግ ማሳየት የምንችለው በምን መንገድ ነው?
1 የአምላክን መንግሥት ምሥራች በማወጁ ሥራ በንቃት በመሳተፍ በተመደብንበት ክልል ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች “መልካም ነገር ከማድረግ” ወደኋላ እንደማንል እናሳያለን። (ምሳሌ 3:27) በአምላክ አገዛዝ ሥር የተሻለ ጊዜ እንደሚመጣ ከመናገር የሚበልጥ ለሰው ዘር የምናካፍለው መልእክት የለም። መደበኛ ባልሆነ መንገድ ምሥክርነት በመስጠት ወይም ጽሑፎችን በማበርከት የመንግሥቱን ተስፋ ለሌሎች እየተናገርክ ቢሆንም እስከ አሁን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መርተህ የማታውቅ ከሆነ እንዲህ ለማድረግ ለምን ግብ አታወጣም?
2. የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ከማስጀመር ወደኋላ እንድንል የሚያደርገን ምን ሊሆን ይችላል?
2 አንዳንድ ጊዜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዳንመራ ትልቅ እንቅፋት የሚሆንብን ለጉዳዩ ያለን አመለካከት ነው። አንዳንዶች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ከመምራት ወደኋላ የሚሉት ብቃት እንደሌላቸው ስለሚሰማቸው ወይም ሕይወታቸው በሥራ የተወጠረ ስለሆነ ነው። ከዚህ ቀጥሎ የቀረቡት ሐሳቦች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በመምራቱ ሥራ ተሳትፎ ከማድረግ ወደኋላ እንዳትል ሊረዱህ ይችላሉ።—ማቴ. 28:19፤ ሥራ 20:20
3. መጽሐፍ ቅዱስን ለማስተማር ብቁ የሆንነው እንዴት ነው?
3 በራስ አለመተማመን:- ምናልባት የትምህርት ደረጃችን ዝቅተኛ በመሆኑ ወይም በሌላ ምክንያት የተነሳ በራስ የመተማመን ስሜት አጥተን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የመምራት ችሎታ እንደሌለን ይሰማን ይሆናል። ውጤታማ አገልጋዮች የነበሩት የመጀመሪያው መቶ ዘመን ክርስቲያኖች “ያልተማሩ ተራ” ሰዎች ነበሩ። ለሌሎች እውነትን እንዲያስተምሩ ያስቻላቸው ምንድን ነው? ‘ከኢየሱስ ጋር የነበሩ’ መሆናቸው ነው። (ሥራ 4:13) እነዚህ ክርስቲያኖች ታላቅ አስተማሪ ከሆነው ከኢየሱስ ተምረው የነበረ ሲሆን የክርስቶስ ትምህርቶችና የማስተማሪያ ዘዴዎች ለእኛ ጥቅም ሲባል በቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ እንዲሰፍሩልን ተደርጓል። የትምህርት ደረጃህ አነስተኛ ቢሆንም እንኳ ፈጽሞ ተወዳዳሪ የሌለው መንፈሳዊ ትምህርት እየቀሰምክ ነው።—ኢሳ. 50:4፤ 2 ቆሮ. 3:5
4. ከአሞጽ ምሳሌ ምን ትምህርት ማግኘት እንችላለን?
4 ይሖዋ የስህተት ጎዳና የተከተሉ ገዥዎችን ወይም ሌሎች ትላልቅ ባለ ሥልጣናትን ለመገሠጽ ነቢያትን የተጠቀመባቸው ጊዜያት ነበሩ። ከእነዚህ ነቢያት መካከል አንዳንዶቹ ከዝቅተኛው የኅብረተሰብ ክፍል የመጡ ነበሩ። ለዚህ አሞጽን እንደ ምሳሌ መጥቀስ እንችላለን። አሞጽ “እኔ እረኛና የባሉጥ ፍሬ ለቃሚ ነኝ እንጂ ነቢይ ወይም የነቢይ ልጅ አይደለሁም” በማለት ሳይሸሽግ ተናግሯል። (አሞጽ 7:14) የሆነ ሆኖ አሞጽ ጥጃ አምላኪ ካህን ለነበረው ለአሜስያስ የይሖዋን የፍርድ መልእክት ከማድረስ ወደኋላ አላለም። (አሞጽ 7:16, 17) የምናከናውነው የአምላክን ሥራ እንደሆነና ለሥራውም ብቁ የሚያደርገን አምላክ ራሱ መሆኑን ምንጊዜም ማስታወስ ይገባናል።—2 ጢሞ. 3:17
5. ሕይወታችን በሥራ የተወጠረ ቢሆንም እንኳ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዲኖረን መጣጣር ያለብን ለምንድን ነው?
5 በሥራ የተወጠረ ሕይወት:- ሕይወትህ በሥራ የተወጠረ ቢሆንም እንኳ ዘወትር በአገልግሎት ለመካፈል ጊዜ መድበህ ሊሆን እንደሚችል ምንም ጥርጥር የለውም። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምራት ከምትደሰትባቸው የአገልግሎት ዘርፎች አንዱ ሊሆን ይችላል። የይሖዋ ቃል በአንድ ግለሰብ ሕይወት ውስጥ የሚያስከትለውን ለውጥ ማየት ትልቅ መብት ነው። (ዕብ. 4:12) አንድ ሰው “እውነትን ወደ ማወቅ” እንዲደርስ ለመርዳት ብለን የምንከፍለው መሥዋዕትነት ይሖዋን ያስደስተዋል። (1 ጢሞ. 2:4) ሌላው ቀርቶ መላእክትም እንኳ አንድ ሰው ከቀድሞ አኗኗሩ ንስሐ ሲገባና መንፈሳዊ እድገት ሲያደርግ ይደሰታሉ።—ሉቃስ 15:10
6. የአምላክን ፈቃድ በማስፈጸም ረገድ ምን ልዩ መብት አግኝተናል?
6 አምላክ “ሰዎች ሁሉ እንዲድኑና እውነትን ወደ ማወቅ እንዲደርሱ” ይፈልጋል። (1 ጢሞ. 2:4) የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለመምራት ወደኋላ ባለማለት ከዚህ የአምላክ ፈቃድ ጋር ተስማምቶ መሥራት እንዴት ያለ ልዩ መብት ነው!