መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ኅዳር 1
“ሰዎች የትሕትናን ባሕርይ ቢያሳዩ ዓለም የተሻለች እንደምትሆን ይሰማዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ኢየሱስ ይህንን ባሕርይ አስመልክቶ ምን እንዳለ ይመልከቱ። [ማቴዎስ 23:12ን አንብብ።] ይህ መጽሔት፣ ትሕትናን ማዳበር ፉክክር በበዛበት በዚህ ዓለም ውስጥ ምን ጠቀሜታ እንዳለው ያብራራል።”
ንቁ! ኅዳር 2007
“ሳይንስ ከፍተኛ እድገት እያደረገ ባለበትና ሰዎች ተጠራጣሪ በሆኑበት በዚህ ዘመን ብዙ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ ጊዜ ያለፈበት እንደሆነ ይሰማቸዋል። እርስዎስ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን አስተያየት አለዎት? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] መጽሐፍ ቅዱስ ሳይንስ ነክ ስለሆኑ ነገሮች የሚናገራቸው ሐሳቦች በሙሉ ትክክል መሆናቸውን ያውቃሉ? [ኢዮብ 26:7ን አንብብ።] ይህ የንቁ! መጽሔት ልዩ እትም በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እምነት እንድንጥል የሚያደርጉንን አሳማኝ ምክንያቶች ይዟል።”
መጠበቂያ ግንብ ኅዳር 15
“ሁላችንም ደስተኛና ትርጉም ያለው ሕይወት መኖር እንፈልጋለን። ኢየሱስ ለደስታ ቁልፍ የሆነውን ነገር አስመልክቶ እዚህ ጥቅስ ላይ በተናገረው ሐሳብ ይስማማሉ? [ማቴዎስ 5:3ን አንብብ። ከዚያም መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ መጽሔት፣ ተፈጥሯዊ ፍላጎታችንን ማለትም አምላክን ለማምለክ ያለንን መሠረታዊ ፍላጎት ማሟላት ሕይወታችን ትርጉም ያለው እንዲሆን የሚያደርገው እንዴት እንደሆነ ያብራራል።”
ንቁ! ታኅሣሥ 2007
“አንዳንዶች ሞት ወደ ሌላ ሕይወት መሸጋገሪያ ድልድይ እንደሆነ ይሰማቸዋል፤ ሌሎች ደግሞ የሰው ልጆች መጨረሻ እንደሆነ ያምናሉ። በእርስዎ አመለካከት ሞት ልንፈራው የሚገባ ነገር ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ኢዮብ ከሞተ በኋላ ስለሚጠብቀው ሁኔታ ምን እንዳለ ይመልከቱ። [ኢዮብ 14:14, 15ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ስንሞት ምን እንደምንሆን መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን ግልጽ ማብራሪያ ይዟል።”