መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል
መጠበቂያ ግንብ ጥቅምት 1
“ሁላችንም ወንጀል፣ ዓመፅና ጦርነት ጠፍቶ ማየት እንናፍቃለን። [መዝሙር 37:11ን አንብብ።] እነዚህ ቃላት ተፈጽመው ለማየት የምንታደል ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥህ ጠብቀው።] ይህ መጽሔት ቀደም ሲል ያነበብኩት የመጽሐፍ ቅዱስ ተስፋ አምላክ ለሰው ዘሮች ከነበረው የመጀመሪያ ዓላማ ጋር ምን ግንኙነት እንዳለውና እኛም ከዚህ በረከት እንዴት ተካፋዮች ለመሆን እንደምንችል ያብራራል።”
ንቁ! ጥቅምት 2004
“አባቶች በልጆቻቸው ሕይወት ውስጥ አንድ ዓይነት ሚና መጫወታቸው ምን ያህል አስፈላጊ ነው ብለው ያስባሉ? [መልስ እስኪሰጥህ ጠብቀው።] ይህ የንቁ! እትም ከጊዜ ወደ ጊዜ አሳሳቢ እየሆነ የመጣውን ያለ አባት የሚያድጉ ልጆች ቁጥር መበራከት በሚመለከት ማብራሪያ ይሰጣል። በተጨማሪም አባቶች በልጆቻቸው ሕይወት ላይ በጎ ተጽዕኖ ማሳደር የሚችሉት እንዴት እንደሆነ ያብራራል።” ምሳሌ 13:1ን አንብብ።
መጠበቂያ ግንብ ጥቅምት 15
“አንዳንድ ሰዎች ብዙ ገንዘብ ካላቸው ሕይወታቸው በደስታ የተሞላ እንደሚሆን ይሰማቸዋል። እርስዎ በዚህ ይስማማሉ? [መልስ እስኪሰጥህ ጠብቀው።] እስቲ አንድ በጣም ሀብታም የነበረ ሰው ምን ብሎ እንደጻፈ ይመልከቱ። [መክብብ 5:10ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ከቁሳዊ ሀብት የበለጠ ዋጋ ስላለው መንፈሳዊ ሀብት ያብራራል።”