መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ጥቅምት 1
“‘እግዚአብሔር አፍቃሪና ሁሉን ቻይ ከሆነ መከራ የሚደርስባቸውን ሰዎች ለማዳን ጣልቃ የማይገባው ለምንድን ነው?’ ብለው ጠይቀው ያውቃሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] በቅርቡ አምላክ በምድር ላይ ያሉትን ችግሮች በሙሉ ያስወግዳል። [ኢሳይያስ 65:17ን አንብብ።] እስከዚያ ድረስ ግን አምላክ መከራ ሲደርስብን በቸልታ ይመለከታል ማለት አይደለም። ይህ መጽሔት ይህንን ጉዳይ ያብራራል።”
ንቁ! ጥቅምት 2003
“ብዙ ሰዎች የብልግና ሥዕሎች በቀላሉ የሚገኙ መሆናቸው ያሳስባቸዋል። ይህ ጉዳይ አሳሳቢ እንደሆነ ይሰማዎታል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠው ጠቃሚ ምክር ከአደጋ ሊጠብቀን ይችላል። [ኤፌሶን 5:3, 4ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ከዚህ ስውር አደጋ ራሳችንን መጠበቅ የምንችልበትን መንገድ ይገልጻል።”
መጠበቂያ ግንብ ጥቅምት 15
“በሕይወት ዘመናችን የምናደርጋቸው አብዛኞቹ ውሳኔዎች በሕይወታችን ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራሉ። የተሳሳተ ውሳኔ እንዳናደርግ ምን ሊረዳን ይችላል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት። ከዚያም ምሳሌ 3:6ን አንብብ።] ይህ የመጠበቂያ ግንብ እትም ጥሩ ውሳኔ ለማድረግ የሚረዱንን በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ አምስት መመሪያዎች ይዟል።”
Oct. 22
“መድኃኒት የሚቋቋሙ ጀርሞች እየተበራከቱ የመምጣታቸው ጉዳይ መነጋገሪያ ርዕስ እንደሆነ ልብ ብለዋል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ይህ መጽሔት መንስኤውን የሚያብራራ ከመሆኑም በላይ ራሳችንን ለመጠበቅ ምን ማድረግ እንደምንችል ሐሳብ ያቀርባል። ከዚህ በተጨማሪም ማንም የማይታመምበት ዓለም እንደሚመጣ የሚናገረውን የመጽሐፍ ቅዱስ ተስፋ ይገልጻል።” ኢሳይያስ 33:24ን አንብብ።