መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ መስከረም 1
“ሁላችንም ደስተኞች ለመሆን እንሻለን። በዚህ ጥቅስ ላይ የተዘረዘሩት ነገሮች በእርግጥ ደስታ የሚያስገኙ ይመስልዎታል? [ማቴዎስ 5:4ሀን፣ 6ሀን እንዲሁም 10ሀን አንብብና መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ይህ መጽሔት ኢየሱስ በዝነኛው የተራራ ስብከቱ ላይ የተናገራቸው እነዚህ አባባሎች ምን ትርጉም እንዳላቸው የሚያብራራ ከመሆኑም በላይ ደስተኛ ለመሆን ምን ተጨማሪ ነገር እንደሚያስፈልግ ይገልጻል።”
ንቁ! መስከረም 2004
“በዘመናችን ወንጀለኞች ሰዎችን ለማጭበርበር በየጊዜው የተለያዩ ዘዴዎችን ይቀይሳሉ። ይህ ሁኔታ ያሳስብዎታል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ይህ የንቁ! እትም እንዳንጭበረበር ሊረዱን የሚችሉ ጥቂት መሠረታዊ ነጥቦችን ያብራራል።” ምሳሌ 22:3ን አንብብ።
መጠበቂያ ግንብ መስከረም 15
“በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በብዙዎች ዘንድ ታዋቂ የሆነውን የሚከተለውን ሐሳብ በጸሎታቸው ውስጥ ያካትታሉ። [ማቴዎስ 6:10ን አንብብ።] የአምላክ ፈቃድ በምድር ላይ ሙሉ በሙሉ ቢፈጸም ሕይወት ምን መልክ የሚኖረው ይመስልዎታል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ይህ መጽሔት ከላይ የተመለከትነውን ሐሳብ ጨምሮ በጌታ ጸሎት ውስጥ የተካተተውን የእያንዳንዱን ልመና ትርጉም ያብራራል።”