መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ መስከ. 1
“ብዙ ሰዎች በዓለማችን ላይ ያሉ ሃይማኖቶች በሙሉ ወደ አንድ ቦታ የሚያደርሱ የተለያዩ መንገዶች እንደሆኑ ይሰማቸዋል። ሌሎች ደግሞ እውነተኛው ሃይማኖት አንድ ብቻ እንደሆነ ያምናሉ። ስለዚህ ጉዳይ አስበው ያውቃሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ይህ መጽሔት በዚህ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ የሚሰጥ አንድ ጥንታዊ ምሳሌ ይዟል።” ማቴዎስ 13:24-30ን አብራራለት።
ንቁ! መስከረም 2003
“ብዙ ሰዎች የዓመጽ ድርጊቶች መባባስ ያስጨንቃቸዋል። [በአካባቢህ የሚታወቅ አንድ ምሳሌ ጥቀስና ሐሳብ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ይህ መጽሔት ለዓመጽ መንስኤ የሚሆኑትን አንዳንድ ምክንያቶች ያብራራል። ከዚህም በላይ አምላክ ወንጀልና ዓመጽን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንደሚያስወግድ ይገልጻል።” መዝሙር 37:10, 11ን አንብብ።
መጠበቂያ ግንብ መስከ. 15
“በዛሬው ጊዜ አንዳንዶች በትዳራቸው ውስጥ ፍቅር እንደጠፋ ይሰማቸዋል። እነዚህ ሰዎች እርዳታ ማግኘት የሚችሉት ከየት ነው? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ የሚሰጣቸው መመሪያዎች ሊጠቅሙን እንደሚችሉ ይገልጻል። [ኢሳይያስ 48:17, 18ን አንብብ።] ይህ የመጠበቂያ ግንብ እትም ጋብቻን ለማጠናከር የሚረዱ የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶችን ያብራራል።”
Sept. 22
“እንስሳት እርስ በርሳቸው የሚግባቡበት መንገድ በጣም አስደናቂ ነው። በዚህ ረገድ የሰው ልጆች ለየት ያለ ተሰጥኦ እንዳላቸው ያውቃሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት። ከዚያም መዝሙር 65:2ን አንብብ።] ከእንስሳት በተለየ መልኩ እኛ ከአምላክ ጋር የመነጋገር ተፈጥሯዊ ፍላጎት አለን። ይህ መጽሔት ከሰዎችም ሆነ ከአምላክ ጋር ጥሩ የሐሳብ ግንኙነት ማድረግ የምንችለው እንዴት እንደሆነ ያብራራል።”