መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ መስከረም 1
“በዘመናችን ታማኝነት የሚወደድ ብዙ ጊዜ ግን የማይተገበር መልካም ባሕርይ ሆኗል። አብዛኞቹ ሰዎች እዚህ ላይ ተጠቅሶ እንደምናገኘው ዓይነት ወዳጅ ቢሆኑ የሚያስደስት አይመስልዎትም? [ምሳሌ 17:17ን አንብብ። ከዚያም መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ መጽሔት ለቤተሰቦቻችንና ለጓደኞቻችን ታማኝ ከሆንን የምናገኛቸውን ጥቅሞች ይናገራል።”
ንቁ! መስከረም 2005
“በርካታ ሰዎች የሰውነት እንቅስቃሴ ለጤንነት አስፈላጊ እንደሆነ ሲነገር የሰሙ ቢሆንም አብዛኞቹ ግን በቂ እንቅስቃሴ እንደማያደርጉ ይናገራሉ። በዚህ አይስማሙም? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ መጽሔት አዘውትሮ የሚደረግ የሰውነት እንቅስቃሴ ያለውን ጠቀሜታ እንዲሁም ሕይወታችን ጥድፊያ የሞላበት ቢሆንም የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግ የምንችልባቸውን አንዳንድ መንገዶች ያብራራል።”
መጠበቂያ ግንብ መስከረም 15
“በምድር ዙሪያ የሚኖሩ ሰዎች ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የተወሰነ እውቀት አላቸው። አንዳንዶች ኢየሱስ ታላቅ ሰው ብቻ እንደሆነ ይሰማቸዋል። ሌሎች ደግሞ ሁሉን ቻይ አምላክ ነው በማለት ያመልኩታል። እርስዎስ ኢየሱስ ክርስቶስ ማን ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ መጽሔት ኢየሱስ ክርስቶስ ማን እንደሆነ፣ ከየት እንደመጣና በአሁኑ ጊዜ የት እንዳለ ይገልጻል።” ዮሐንስ 17:3ን አንብብ።