መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ጥቅምት 1
“የሥነ ሕይወት ተመራማሪዎች በሽታን ለማስወገድና ዕድሜያችንን ለማራዘም ጥረት እያደረጉ ነው። ይዋል ይደር እንጂ ለዘላለም መኖር የሚቻልበት ጊዜ እንደሚመጣ አስበው ያውቃሉ? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ረጅም ዕድሜ መኖር የምንመኘው ለምን እንደሆነ እስቲ ይመልከቱ። [መክብብ 3:11ን አንብብ።] አምላክ ሲፈጥረን ለዘላለም የመኖር ፍላጎትን የሰጠን ለምን እንደሆነ ይህ መጽሔት ያብራራል።”
ንቁ! ጥቅምት 2006
“አብዛኞቻችን የምንወዳቸውን ሰዎች በሞት አጥተናል። ታዲያ ከሞቱ በኋላም ቢሆን እነርሱን ለመርዳት ማድረግ የምንችለው ነገር እንዳለ ይሰማዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ ርዕስ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ለዚህ ጥያቄ የሚሰጠውን መልስ ይዟል። ከዚህም በላይ ይህንን የሚያጽናና ተስፋ ያብራራል።” ዮሐንስ 5:28, 29ን አንብብ። ከዚያም በገጽ 10 ላይ ያለውን ርዕስ አስተዋውቀው።
መጠበቂያ ግንብ ጥቅምት 15
“አንዳንድ ሰዎች፣ አምላክ የሚኖረው በሰማይ ስለሆነ እርሱን ማወቅ አይቻልም የሚል መደምደሚያ ላይ ደርሰዋል። እርስዎስ እንደዚህ ይሰማዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው። ከዚያም ዮሐንስ 17:3ን አንብብ።] ይህ መጽሔት አምላክን ማወቅ የምንችለው እንዴት እንደሆነ ያብራራል።”
ንቁ! ኅዳር 2006
“አፍቃሪ፣ ፍትሐዊና ኃያል የሆነ አምላክ ካለ ብዙ መከራና ሥቃይ የኖረው ለምን እንደሆነ ጠይቀው ያውቃሉ? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ ጥቅስ የመከራ መንስኤ የሆነውን አካል በተመለከተ ምን እንደሚል ይመልከቱ። [1 ዮሐንስ 5:19ን አንብብ።] ይህ መጽሔት አምላክ የሰው ልጆችን ሥቃይ ለማስወገድ ያደረገውን ዝግጅት ከመጽሐፍ ቅዱስ ያብራራል።”