መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ጥቅምት 1
“አባት በቤተሰብ ሕይወት ውስጥ ትልቅ ድርሻ እንዳለው ምሑራን አምነውበታል። አንድን ሰው ጥሩ አባት የሚያስብለው ምን ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ኢየሱስ የአባቱ ምሳሌነት እንዴት እንደረዳው ጎላ አድርጎ ገልጿል። [ዮሐንስ 5:19ን አንብብ።] ይህ ርዕስ አንድ አባት ማድረግ የሚኖርበትን ስድስት አስፈላጊ ነገሮች ያብራራል።” ገጽ 18 ላይ የሚጀምረውን ርዕስ አሳየው።
ንቁ! ጥቅምት 2008
“በተለያዩ ሃይማኖቶች ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ስለ አምላክ ምንነት እርስ በርሱ የሚጋጭ አመለካከት አላቸው። ይሁንና የአምላክ ልጅ ስለ አባቱ ምን ብሏል? በዮሐንስ 4:24 ላይ ኢየሱስ ምን እንዳለ ልብ ይበሉ። [ጥቅሱን አንብብ።] ይህ ርዕስ ‘ስለ አምላክ ምንነት ምን ማለት ይቻላል?’ የሚለውን ጥያቄ አስመልክቶ መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል ከሁለት በማይበልጡ ገጾች ያብራራል።” ገጽ 24 እና 25 ላይ የሚገኘውን ርዕስ አሳየው።
መጠበቂያ ግንብ ኅዳር 1
“ባሎችም ሆኑ ሚስቶች ይህን የመጽሐፍ ቅዱስ ምክር ተግባራዊ ቢያደርጉ የጋብቻ ጥምረታቸው የሚጠናከር አይመስልዎትም? [ኢዮብ 31:1ን አንብብ። ከዚያም መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ ርዕስ ባለትዳሮች የጋብቻ ቃል ኪዳናቸውን አክብረው እንዲኖሩ የሚረዷቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎች ያብራራል።” ገጽ 18 ላይ የሚጀምረውን ርዕስ አሳየው።
ንቁ! ኅዳር 2008
“‘ስኬታማ መሆን የምትችለው እንዴት ነው?’ በሚለው ጥያቄ ዙሪያ ሰዎች ጥሩ ግንዛቤ እንዲኖራቸው እየረዳን ነው። [ሽፋኑ ላይ ያለውን ርዕስ አሳየው።] ብዙዎች ስኬትን በተመለከተ ትክክለኛ አመለካከት ያላቸው ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] እባክዎ፣ አንድ ጥቅስ ላንብብልዎ። [መዝሙር 1:1, 3ን አንብብ።] ጥሩ ሥነ ምግባር መያዝና ከአምላክ ጋር ወዳጅነት መመሥረት ስኬታማ ከመሆን ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ሳያስተውሉ አይቀሩም። በዚህ መጽሔት ገጽ 6 ላይ በሚገኘው ‘ስኬታማ ለመሆን የሚረዱ ስድስት መንገዶች’ በሚለው ርዕስ ሥር ተጨማሪ ሐሳቦችን ማግኘት ይችላሉ።”