መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ጥቅምት 1
“‘ምናለ እንዲህ ባላደረግሁ ኖሮ!’ ብለው ተቆጭተው ያውቃሉ? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ሁላችንም አልፎ አልፎ የኋላ ኋላ የምንጸጸትበትን ምርጫ የምናደርግበትን ምክንያት በተመለከተ ይህ ጥቅስ ምን እንደሚል ይመልከቱ። [ኤርምያስ 10:23ን አንብብ።] ይህ መጽሔት፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙት ተግባራዊ ምክሮች ጥሩ ምርጫ እንድናደርግ የሚረዱን እንዴት እንደሆነ ያብራራል።”
ንቁ! ጥቅምት 2007
“ሁላችንም የምንወዳቸውን ሰዎች በሞት አጥተናል። እነዚህ ሰዎች ከሰማይ ሆነው የሚመለከቱን ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ኢየሱስ፣ አልዓዛር በሞተበት ወቅት ምን እንዳለ ይመልከቱ። [ዮሐንስ 11:11ን አንብብ።] ይህ ርዕስ ሙታን በአንድ በሆነ ቦታ በሕይወት እየኖሩ ነው ወይስ ከሕልውና ውጭ ሆነው ትንሣኤ የሚያገኙበትን ጊዜ ይጠብቃሉ ለሚለው ጥያቄ ማብራሪያ ይሰጣል።” በገጽ 28 ላይ የሚገኘውን ርዕስ አሳየው።
መጠበቂያ ግንብ ጥቅምት 15
“ብዙ ሰዎች የወደፊቱ ጊዜ የማያስተማምን ከመሆኑ የተነሳ ለዛሬ ብቻ መኖሩ የተሻለ እንደሆነ ይሰማቸዋል። እርስዎ ይህን በሚመለከት ምን ይላሉ? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ኢየሱስ ትኩረት የሚስብ ሐሳብ ተናግሯል። [ማቴዎስ 6:34ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ስለ ወደፊቱ ጊዜ ከልክ በላይ ሳንጨነቅ ለነገ እቅድ ማውጣት የምንችለው እንዴት እንደሆነ ያብራራል።”
ንቁ! ኅዳር 2007
“ቀደም ባሉት ጊዜያት ሰዎች መመሪያ ለማግኘት ብዙውን ጊዜ ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ዘወር ይሉ ነበር። በዛሬው ጊዜ ግን ብዙ ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ጥርጣሬ እንዳላቸው ሲናገሩ ይደመጣል። እርስዎ ምን ይሰማዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው። ከዚያም 2 ጢሞቴዎስ 3:16ን አንብብ።] ይህ የንቁ! መጽሔት ልዩ እትም መጽሐፍ ቅዱስ በአምላክ መንፈስ አነሳሽነት የተጻፈ መጽሐፍ መሆኑን የሚያሳዩ አሳማኝ ማስረጃዎችን ይዟል።”