መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ጥቅምት 1
“ብዙዎች ዛሬ የምንመለከታቸው እንደ ጦርነት፣ ወንጀል እና ሽብርተኝነት ያሉ ችግሮች የሚወገዱበት ጊዜ ይመጣ ይሆን ብለው ያስባሉ። እርስዎስ ስለዚህ ጉዳይ ምን ይሰማዎታል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] መጽሐፍ ቅዱስ የሚከተለውን የሚያጽናና ተስፋ ይሰጣል። [መዝሙር 37:10, 11ን አንብብ።] ይህ መጽሔት አምላክ ክፋትንና በክፋት ድርጊቶች ሳቢያ የሚመጣውን መከራና ስቃይ ለመታገስ የመረጠበትን ምክንያት ያብራራል።”
ንቁ! ጥቅምት 2002
“ከአካባቢ ብክለት ጋር የተያያዙ ችግሮችን የሰው ልጅ መፍትሔ ያገኝላቸዋል ብለው ያስባሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] የችግሩ ዋነኛ መንስኤ አባካኝነት ነው። ኢየሱስ ተከታዮቹ አባካኞች እንዳይሆኑ አስተምሯቸዋል። [ዮሐንስ 6:12ን አንብብ።] የመጽሐፍ ቅዱስን መመሪያ መከተል ቤተሰቦች የመጣል አባዜ የተጠናወተውን ኅብረተሰብ እንዳይመስሉ እንዴት ሊረዳቸው እንደሚችል ይህ መጽሔት ያሳያል።”
መጠበቂያ ግንብ ጥቅምት 15
“በዛሬው ጊዜ ክፋት የበዛበትን ምክንያት ለልጆች ወይም ለሌሎች ሰዎች እንዴት ብለው ያስረዳሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] መጽሐፍ ቅዱስ ‘ከክፋት ሁሉ በስተጀርባ ያለው ማን ነው?’ ለሚለው ጥያቄ መልስ ይሰጣል። [1 ዮሐንስ 5:19ን አንብብ።] ይህ የመጠበቂያ ግንብ እትም ይህ ክፉ ፍጡር ማን እንደሆነና እንዴት ልንቋቋመው እንደምንችል እንዲገነዘቡ ይረዳዎታል።”
Oct. 8
“ሃይማኖታዊ መሪዎች ወይም ሌሎች ሰዎች የሚያቀርቧቸው ጸሎቶች ለዓለም ሰላም ያመጣሉ ብለው ያስባሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] መጽሐፍ ቅዱስ በዓለም ዙሪያ ሰላም የሚሰፍንበት ጊዜ እንደሚመጣ ይናገራል። [ኢሳይያስ 9:6, 7ን አንብብ።] ለዓለም ሰላም የሚያመጣ አንድ ልዩ ገዢ እንዳለ ከዚህ ጥቅስ ልብ ብለዋል? በዚህ የንቁ! እትም ላይ ይህ ገዢ ማን እንደሆነና እውነተኛ ሰላም የሚያመጣው እንዴት እንደሆነ ተብራርቷል።”