የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 11/08 ገጽ 8
  • አስተማሪ መሆን ትችላለህ!

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አስተማሪ መሆን ትችላለህ!
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ሌሎችን ማሠልጠን አስፈላጊ እንደሆነ ይሰማሃል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016
  • የመንግሥቱን አገልጋዮች ማሠልጠን
    የአምላክ መንግሥት እየገዛ ነው!
  • ይሖዋ ለዚህ ሥራ ሥልጠና እየሰጠን ነው
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2011
  • የማስተማርን ችሎታ ማዳበር
    ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
km 11/08 ገጽ 8

አስተማሪ መሆን ትችላለህ!

1. እያንዳንዱ የመንግሥቱ አስፋፊ ምን የማድረግ ልዩ አጋጣሚ አለው?

1 አገልግሎትን በጣም አስደሳች ከሚያደርጉት ነገሮች መካከል ለሰዎች እውነትን ማስተማር ይገኝበታል። የምናስተምረው ሰው ለመንግሥቱ መልእክት በጎ ምላሽ ሲሰጥ ማየትና ወደ አጽናፈ ዓለሙ ሉዓላዊ ጌታ እንዲቀርብ መርዳት ትልቅ መብት ነው። (ያዕ. 4:8) እያንዳንዱ የመንግሥቱ አስፋፊ እውነትን የተጠማ ሰው የማስተማር እንዲሁም ግለሰቡ በባሕርይው፣ በአመለካከቱና በአኗኗሩ ላይ ትልቅ ለውጥ ማድረግ እንዲችል የመርዳት ግብ ሊኖረው ይገባል።—ማቴ. 28:19, 20

2. አንዳንዶች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ከመምራት ወደኋላ የሚሉት ለምን ሊሆን ይችላል? ይህን ችግር ለማሸነፍስ ምን ይረዳቸዋል?

2 በይሖዋ ታመን፦ በጥንት ጊዜ የኖሩ ታማኝ የአምላክ አገልጋዮች ይሖዋ የሰጣቸውን ተልእኮ ለመወጣት ብቃቱ እንደሌላቸው ተሰምቷቸው ነበር። ሙሴ፣ ኤርምያስ፣ አሞጽና ሌሎች ተራ ሰዎች በይሖዋ አምላክ መታመናቸው የነበራቸውን ጥርጣሬና ስጋት እንዲያሸንፉ እንዲሁም ትልቅ ትርጉም ያለው ሥራ እንዲያከናውኑ አስችሏቸዋል። (ዘፀ. 4:10-12፤ ኤር. 1:6,7፤ አሞጽ 7:14, 15) ሐዋርያው ጳውሎስም ‘ድፍረት ማግኘት’ አስፈልጎት ነበር። ታዲያ ድፍረት ያገኘው እንዴት ነበር? “በአምላካችን” እርዳታ እንደሆነ ገልጿል። (1 ተሰ. 2:2) አዎን፣ ውጤታማ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች መምራት እንድንችል የሚያስፈልገንን እርዳታ፣ ጥበብና ኃይል ለማግኘት ሁላችንም በይሖዋ መታመን እንችላለን።—ኢሳ. 41:10፤ 1 ቆሮ. 1:26, 27፤ 1 ጴጥ. 4:11

3, 4. የአምላክን ቃል በማስተማር ረገድ ሥልጠና የምናገኝበት ምን ዝግጅት አለ?

3 የሚሰጥህን ሥልጠና ተቀበል፦ ታላቁ አስተማሪያችን ይሖዋ አምላክ በማያቋርጥ መንፈሳዊ የትምህርት መርሐ ግብር አማካኝነት የተሟላ ብቃት ያለን አስተማሪዎች እንድንሆን ሥልጠና ይሰጠናል። (ኢሳ. 54:13፤ 2 ጢሞ. 3:16, 17) የቅዱሳን መጻሕፍት እውቀትህን ለማሳደግ እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችን የማስተማር ችሎታህን ለማሻሻል በሚረዱህ በእነዚህ ዝግጅቶች የቻልከውን ያህል በመጠቀም የሚሰጥህን ሥልጠና ተቀበል። ውጤታማ አስተማሪዎች እንድንሆን በዋነኝነት የሚረዱን ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት እና የአገልግሎት ስብሰባዎች ቢሆኑም ሁሉም የጉባኤ ስብሰባዎች ከአምላክ ቃል እንድናስተምር ያሠለጥኑናል።

4 ጥልቅ የሆኑ መንፈሳዊ እውነቶችን እንኳ ሳይቀር ቀላል በሆነ መንገድ እንዴት ማስተማር እንደምትችል ለማወቅ ጥረት አድርግ። በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ገጽ 227 ላይ “ትምህርቱ ለአድማጮችህ ግልጽ እንዲሆንላቸው ከፈለግህ በቅድሚያ ለአንተ ለራስህ ግልጽ ሊሆንልህ ይገባል” የሚል ሐሳብ ይገኛል። በስብሰባዎች ላይ ሐሳብ መስጠት ወደፊት ልንጠቀምባቸው የምንፈልጋቸው ዋና ዋና ነጥቦች በአእምሯችን ላይ እንዲቀረጹ ያደርጋል። በመሆኑም በደንብ ተዘጋጅ፤ ይህን ካደረግህ በማስተማር ችሎታህ ረገድ ያለህ የእርግጠኝነት ስሜት እያደገ ይሄዳል።

5. የማስተማር ችሎታችንን ለማሻሻል የሚረዳ ምን ተጨማሪ ሥልጠና እናገኛለን?

5 ጥንትም ቢሆን ክርስቲያን አገልጋዮች ደቀ መዛሙርት በማድረጉ ሥራ ሲካፈሉ አንዳቸው ከሌላው ትምህርት ይቀስሙ እንደነበር ምንም ጥርጥር የለውም። (ሉቃስ 10:1) የሚቻል ከሆነ አቅኚዎችን፣ ሽማግሌዎችንና ተጓዥ የበላይ ተመልካቾችን ጨምሮ ተሞክሮ ያላቸው አስፋፊዎች መጽሐፍ ቅዱስ ሲያስጠኑ በጥናቱ ላይ ተገኝ። ከዚያም ቅዱስ ጽሑፋዊ እውነቶችን ለማብራራት በማስጠኛ ጽሑፎቻችን ላይ እንደሚገኙት ሥዕሎችና ቀላል ምሳሌዎች ያሉ የማስተማሪያ መሣሪያዎችን እንዴት እንደሚጠቀሙባቸው ልብ በል። የተሻለ አስተማሪ መሆን የምትችለው እንዴት እንደሆነ ሐሳብ እንዲሰጡህ ጠይቃቸው። (ምሳሌ 1:5፤ 27:17) አምላክ ሥልጠና የሚሰጥበት አንዱ መንገድ ይህ ስለሆነ ከወንድሞችና ከእህቶች ለምታገኘው ሥልጠና አመስጋኝ ሁን።—2 ቆሮ. 3:5

6. የአምላክ ቃል አስተማሪ ለመሆን የሚያስፈልገው ወሳኝ ነገር ምንድን ነው?

6 በይሖዋ ታመን፤ እንዲሁም እሱ ከሚያቀርበው ሥልጠና ተጠቀም። እድገት ማድረግ እንድትችል አዘውትረህ ጸልይ። (መዝ. 25:4, 5) ሌሎችም ልክ እንደ አንተ የአምላክ ቃል አስተማሪ እንዲሆኑ መርዳት የሚያስገኘውን ደስታ አንተም መቅመስ ትችላለህ!

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ