የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 8/09 ገጽ 9
  • የ2010 የልዩ ስብሰባ ቀን ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የ2010 የልዩ ስብሰባ ቀን ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2009
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ‘በተገቢው ጊዜ የቀረበ ምግብ’
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2010
  • የወረዳና የልዩ ስብሰባዎችን ለመከለስ የተደረገ አዲስ ዝግጅት
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
  • የአምላክ ቃል ኃይለኛ ነው
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2013
  • አዲስ የልዩ ስብሰባ ቀን ፕሮግራም
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2009
km 8/09 ገጽ 9

የ2010 የልዩ ስብሰባ ቀን ፕሮግራም

1. (ሀ) በቅርቡ ዓመታት ካደረግናቸው ልዩ ስብሰባዎች መካከል ጥቂቶቹ የትኞቹ ናቸው? (ለ) ቀደም ሲል ካደረግናቸው የልዩ ስብሰባ ቀኖች በአገልግሎታችሁ የረዷችሁ ምን የምታስታውሷቸው ነጥቦች አሉ?

1 “ይበልጥ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ለይታችሁ እወቁ፣” “እንደ አንድ መንጋ ሆናችሁ ጸንታችሁ ቁሙ፣” “ስለ እውነት መመሥከራችሁን ቀጥሉ” እና “እኛ ሸክላዎች፣ ይሖዋ ደግሞ ሠሪያችን ነው።” (ፊልጵ. 1:9, 10, 27፤ ዮሐ. 18:37፤ ኢሳ. 64:8) እነዚህ ባለፉት ዓመታት ከወሰድናቸው በርካታ የልዩ ስብሰባ ጭብጦች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው። በ2010 የአገልግሎት ዓመት በሚካሄደው የልዩ ስብሰባ ቀን ላይ ለመገኘት ጓጉታችኋል? ይህ የልዩ ስብሰባ ቀን በ1 ቆሮንቶስ 7:29 ላይ የተመሠረተውን “የቀረው ጊዜ አጭር ነው” የሚለውን ጭብጥ የሚያብራራ ነው።

2. በዚህ ልዩ ስብሰባ ላይ ለመገኘት ጉጉት እንዲያድርብን ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?

2 የልዩ ስብሰባውን መቼ እንደምታደርጉ በጉባኤ ማስታወቂያ ከተነገረበት ጊዜ አንስቶ ስብሰባውን በጉጉት መጠበቅ እንድትችሉ አንዳንድ ነገሮችን እያነሳችሁ ተወያዩ። አንዳንድ ወላጆች ልጆቻቸው በስብሰባው ላይ ለመገኘት ጉጉት እንዲያድርባቸው ለማድረግ ቀኑንና ለዕለቱ የሚያስፈልጓቸውን ነገሮችን በቀን መቁጠሪያቸው ላይ የሚጽፉ ከመሆኑም ሌላ ‘ይሄን ያህል ቀን ቀረው’ እያሉ አንዳቸው ሌላውን ያስታውሳሉ። የቤተሰብ አምልኮ በምታደርጉበት ምሽት ላይ ቀደም ሲል በተደረጉት የልዩ ስብሰባ ቀኖች ላይ የያዛችሁትን ማስታወሻ መከለስ ትችላላችሁ። በተጨማሪም በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም በተባለው መጽሐፍ ገጽ 13-16 ላይ የሚገኘውን “እንዴት እንደምታዳምጡ በጥንቃቄ አስቡ” የሚለውን ርዕስ በመከለስ ልባችሁን ማዘጋጀት ትችላላችሁ።—ሉቃስ 8:18

3. ከስብሰባው የተሟላ ጥቅም ማግኘት የምንችለው እንዴት ነው?

3 የተማራችሁትን በተግባር አውሉ፦ አንድ ልዩ ስብሰባ ካለቀ በኋላ ብዙዎች “ግሩም ስብሰባ ነበር!” ሲሉ መስማት የተለመደ ነው። ይህ ስብሰባ ይሖዋ ካደረገልን በመንፈሳዊ ከሚያበለጽጉን በርካታ ዝግጅቶች መካከል አንዱ እንደመሆኑ መጠን ግሩም መሆኑ ምንም ጥያቄ የለውም። (ምሳሌ 10:22) የቀሰምነው ትምህርት ፍሬ እንዲያፈራ ከተፈለገ በተማርነው ነገር ላይ ማሰላሰልና ያገኘነውን እውቀት በውስጣችን ማኖር ይገባናል። (ሉቃስ 8:15) ከስብሰባው በኋላ ወደ ቤት ስትሄዱ ከቤተሰባችሁ አሊያም በመኪና አብረዋችሁ ከሚጓዙት ጋር ስለ ፕሮግራሙ ተወያዩ። ስላወጣችኋቸው ግቦች እርስ በርስ ተነጋገሩ እንዲሁም ለአገልግሎታችሁ የሚጠቅሟችሁን ነጥቦች አንስታችሁ ተወያዩ። እንዲህ ማድረጋችሁ ስብሰባው ካለፈ ከብዙ ጊዜ በኋላም ከትምህርቱ ተጠቃሚ እንድትሆኑ ይረዳችኋል።—ያዕ. 1:25

4. ይህን ልዩ ስብሰባ ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው?

4 ስንመኘው የኖርነውን እጅግ ጠቃሚ የሆነ ስጦታ ስንቀበል ልዩ ስሜት እንደሚያድርብን ግልጽ ነው። ታዲያ ይሖዋ በቅርቡ በልዩ ስብሰባ አማካኝነት ሊሰጠን ያዘጋጀልንን ስጦታ በጉጉት ልንጠብቀው አይገባም? ስብሰባው በሁሉም የሕይወት ዘርፋችን እንደሚጠቅመን እርግጠኞች መሆን እንችላለን። የሰማዩ አባታችን ይሖዋ አበረታች በሆኑ ትምህርቶችና የሰጠንን ሥራ ለማከናወን በሚያስችሉን ሥልጠናዎች አማካኝነት ትክክለኛውን ስጦታ እንደሚያበረክትልን መጠበቅ እንችላለን።—2 ጢሞ. 4:2፤ ያዕ. 1:17

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ