የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 7/10 ገጽ 2
  • የምችለውን ያህል እያደረግኩ ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የምችለውን ያህል እያደረግኩ ነው?
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2010
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ለይሖዋ ማሳሰቢያዎች ልባዊ ፍቅር አላችሁን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
  • የይሖዋ ማሳሰቢያዎች እምነት የሚጣልባቸው ናቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • የይሖዋ ማሳሰቢያዎች በመንፈሳዊ እያነቃቁን ነውን?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
  • ልባችሁ በይሖዋ ማሳሰቢያዎች ሐሴት ያድርግ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2010
km 7/10 ገጽ 2

የምችለውን ያህል እያደረግኩ ነው?

1. አንድን ታማኝ ክርስቲያን ምን ነገሮች ሊያሳስቡት ይችላሉ?

1 ከላይ ያለውን ጥያቄ ራስህን ጠይቀህ ታውቃለህ? ምናልባትም በዕድሜ መግፋት፣ በጤና ችግር ወይም የቤተሰብ ኃላፊነቶችህ በመጨመራቸው ምክንያት በአገልግሎት የምታደርገው ተሳትፎ መቀነሱ ተስፋ አስቆራጭ ሆኖብህ ይሆናል። የሦስት ልጆች እናት የሆነች አንዲት እህት ቤተሰቧን መንከባከብ ብዙ ጊዜና ጉልበት የሚጠይቅባት መሆኑ በአገልግሎት እንደ ልቧ እንዳትካፈል ስላደረጋት አንዳንዴ የጥፋተኝነት ስሜት እንደሚሰማት ጽፋለች። እንዲህ ያሉ ጉዳዮችን ሚዛናዊ በሆነ መልኩ ለመመልከት ምን ሊረዳን ይችላል?

2. ይሖዋ ከእኛ የሚጠብቀው ምንድን ነው?

2 ይሖዋ ከእኛ የሚጠብቀው ምንድን ነው? ሁላችንም በአገልግሎት ላይ የምናደርገውን ተሳትፎ ማሳደግ ብንችል ደስ እንደሚለን የታወቀ ነው። ይሁንና ብዙውን ጊዜ ልናደርግ በምንፈልገው እና ማድረግ በምንችለው ነገር መካከል ትልቅ ልዩነት አለ። እንደ እውነቱ ከሆነ ከአሁኑ የበለጠ ለማድረግ መፈለጋችን ግድየለሽ አለመሆናችንን ይጠቁማል። ይሖዋ ያለብንን የአቅም ገደብ በደንብ እንደሚያውቅና ከአቅማችን በላይ እንደማይጠብቅብን ማስታወስ ይኖርብናል። (መዝ. 103:13, 14) ታዲያ ከእኛ የሚጠብቀው ምንድን ነው? ይሖዋ ምርጣችንን በመስጠት በሙሉ ነፍሳችን እንድናገለግለው ይፈልጋል።—ቆላ. 3:23

3. በአገልግሎት ላይ የምናደርገውን ተሳትፎ መመርመር የምንችለው እንዴት ነው?

3 ማድረግ የምንችለው ምን ያህል እንደሆነ ለማወቅ ምን ሊረዳን ይችላል? ያለንበትን ሁኔታ በትክክል መገንዘብ እንድንችል እንዲረዳን ይሖዋን ልንጠይቀው እንችላለን። (መዝ. 26:2) በተጨማሪም ሁኔታችንን በሚገባ የሚያውቅ እንዲሁም ማሻሻል ያለብንን ነገር በግልጽ የሚነግረን ታማኝና ጎልማሳ ክርስቲያን ጓደኛ ካለን በዚህ ረገድ ሊረዳን ይችላል። (ምሳሌ 27:9) ሁኔታዎች ስለሚለዋወጡ ያለንበትን ሁኔታ በየጊዜው መመርመራችን ጠቃሚ መሆኑን ማስታወስ አለብን።—ኤፌ. 5:10

4. አገልግሎትን በተመለከተ የሚሰጡንን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማሳሰቢያዎች እንዴት ልንመለከታቸው ይገባል?

4 ለሚሰጠን ማሳሰቢያ ሊኖረን የሚገባው አመለካከት፦ የሩጫ ውድድር ሲካሄድ ደጋፊዎች ሯጮቹን ለማበረታታት ብዙውን ጊዜ ይጮሃሉ። የሚጮኹት ሯጮቹ እንዲያሸንፉ ለማበረታታት እንጂ ተስፋ ለማስቆረጥ አይደለም። በተመሳሳይም በስብሰባዎችና በጽሑፎች ላይ ‘ቃሉን በጥድፊያ ስሜት እንድንሰብክ’ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማበረታቻና ማሳሰቢያ የሚሰጠን የምናደርገው ጥረት በቂ እንዳልሆነ ለመግለጽ ሳይሆን እኛን ለመርዳት ታስቦ ነው። (2 ጢሞ. 4:2) ምርጣችንን ለይሖዋ ለመስጠት ጥረት ማድረጋችንን እስከቀጠልን ድረስ ይሖዋ ‘ፍቅራችንንና ሥራችንን’ እንደሚያስታውስና ልቡም በደስታ እንደሚሞላ እርግጠኞች መሆን እንችላለን።—ዕብ. 6:10

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ