ከአሁን በኋላ የመስክ ስምሪት ስብሰባዎችን ለመምራት በዕለት ጥቅስ አንጠቀምም
ከዚህ ቀደም የዕለት ጥቅሱ ከአገልግሎት ጋር የተያያዙ ነጥቦች ካሉት በመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባዎች ላይ ሊቀርብ ይችል ነበር። አሁን ግን በዚህ ረገድ ለውጥ ተደርጓል። ከአሁን በኋላ የመስክ አገልግሎት ስብሰባዎችን ለመምራት ቅዱሳን መጻሕፍትን በየዕለቱ መመርመር በተባለው ቡክሌት መጠቀም የለብንም። እንደ በፊቱ ሁሉ ስብሰባውን የሚመራው ወንድም መጽሐፍ ቅዱስን፣ የመንግሥት አገልግሎታችንን፣ የአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍን፣ ማመራመርን እንዲሁም ከአገልግሎት ጋር ተያያዥነት ያላቸው ሌሎች ጽሑፎችን መጠቀም ይችላል። ስብሰባውን እንዲመሩ የተመደቡት ወንድሞች በዕለቱ ወደ አገልግሎት ለመሄድ የሚመጡትን አስፋፊዎች ሊጠቅም የሚችል ተግባራዊ ነጥብ ለማካፈል ዝግጅት ማድረግ ይኖርባቸዋል። ከዚህ በፊት እንደሚደረገው ሁሉ ስብሰባው ከ10 እስከ 15 ደቂቃዎች መብለጥ የለበትም፤ በተለይ ከጉባኤ ስብሰባ ቀጥሎ የሚደረግ ከሆነ የስምሪት ስብሰባው የበለጠ ማጠር ይኖርበታል።