የጥያቄ ሣጥን
◼ ጥሩ እድገት እያደረገ ካለ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪ ጋር ማጥናት ያለብን ለምን ያህል ጊዜ ነው?
ጥሩ እድገት እያደረገ ያለ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? እና ‘ከአምላክ ፍቅር አትውጡ’ የተባሉትን ጽሑፎች አጥንቶ እስኪጨርስ ድረስ ማጥናቱን ቢቀጥል የተሻለ ነው። ተማሪው እነዚህን መጻሕፍት አጥንቶ ከመጨረሱ በፊት ቢጠመቅ እንኳ ጥናቱን መቀጠል ይኖርበታል። ግለሰቡ ከተጠመቀም በኋላ ሰዓቱን፣ ተመላልሶ መጠየቆችንና ጥናቱን ሪፖርት ማድረጋችንን መቀጠል እንችላለን። በጥናቱ ወቅት ሌላ አስፋፊ ከተገኘ እሱም ሰዓት መያዝ ይችላል።—የመጋቢት 2009 የመንግሥት አገልግሎታችንን ገጽ 2 ተመልከት።
አዲሶች ጥናታቸውን ከማቆማቸው በፊት በእውነት ውስጥ ጥሩ መሠረት ሊኖራቸው ይገባል። ወደፊት የሚያጋጥማቸውን መከራ መቋቋም እንዲችሉ በክርስቶስ ላይ ‘መተከልና በእምነት ጸንተው መኖር’ ያስፈልጋቸዋል። (ቆላ. 2:6, 7፤ 2 ጢሞ. 3:12፤ 1 ጴጥ. 5:8, 9) በተጨማሪም ሌሎችን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለማስተማር “የእውነትን ትክክለኛ እውቀት” ማግኘት ያስፈልጋቸዋል። (1 ጢሞ. 2:4) ጥናቶቻችንን ሁለቱንም መጽሐፍ የምናስጠናቸው ከሆነ ‘ወደ ሕይወት ከሚወስደው መንገድ’ እንዳይወጡ እየረዳናቸው ነው።—ማቴ. 7:14
ሽማግሌዎች አንድ ሰው እንዲጠመቅ ከመፍቀዳቸው በፊት መሠረታዊ የሆኑትን የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች በሚገባ መረዳቱንና አኗኗሩ ከዚህ ጋር የሚስማማ መሆኑን ማረጋገጥ አለባቸው። ሽማግሌዎች በተለይ የመጀመሪያውን የማጥኛ መጽሐፍ ያልጨረሱ ጥናቶች ለመጠመቅ የሚያቀርቡትን ጥያቄ ሲያዩ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው። አንድ ሰው ለመጠመቅ ብቁ ካልሆነ ሽማግሌዎቹ ግለሰቡ ወደፊት ብቁ ለመሆን የሚያስችለውን እርዳታ እንዲያገኝ ሁኔታውን ማመቻቸት ይኖርባቸዋል።—የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ፣ ከገጽ 216-218 ተመልከት።
[በገጽ 2 ላይ የሚገኝ የተቀነጨበ ሐሳብ]
አዲሶች . . . በእውነት ውስጥ ጥሩ መሠረት ሊኖራቸው ይገባል