‘በእምነት ጸንተው እንዲኖሩ’ እርዷቸው
በየዓመቱ ከሩብ ሚሊዮን የሚበልጡ ሰዎች ይጠመቃሉ፤ ይሖዋ ሰዎችን የመሰብሰቡን ይህን ሥራ በዚህ መልኩ እየባረከው እንደሆነ መመልከት በጣም ያስደስታል። (ዘዳ. 28:2) አስፋፊዎች፣ ጥናታቸው ከተጠመቀ በኋላ እሱን ማስጠናታቸውን አቁመው ትኩረታቸውን ሌሎችን በመርዳት ላይ የማድረግ ዝንባሌ እንዳላቸው ይታያል። ተማሪውም ቢሆን ለአገልግሎት የሚሆን ተጨማሪ ጊዜ ለማግኘት ሲል ጥናቱን ማቆም ይፈልግ ይሆናል። ይሁን እንጂ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች በእውነት ውስጥ ጥሩ መሠረት ሊኖራቸው ይገባል። በክርስቶስ ላይ ‘መተከልና በእምነት ጸንተው መኖር’ ያስፈልጋቸዋል። (ቆላ. 2:6, 7፤ 2 ጢሞ. 3:12) በመሆኑም አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪ ቢጠመቅም እንኳ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት እና ‘ከአምላክ ፍቅር አትውጡ’ የተባሉትን መጽሐፎች አጥንቶ መጨረስ አለበት።—የሚያዝያ 2011 የመንግሥት አገልግሎታችንን ገጽ 2 ተመልከት።