በመጠበቂያ ግንብ ላይ የሚወጣ አዲስ ዓምድ
በወሩ የመጀመሪያ ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር መጠበቂያ ግንብ ላይ የሚወጣውን “ከአምላክ ቃል ተማር” የተባለውን ዓምድ ስንጠቀም ቆይተናል። ከጥር ወር ጀምሮ ግን ይህ ዓምድ “የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው” በሚል አዲስ ዓምድ የሚተካ ሲሆን ይህም ለሕዝብ በሚሰራጨው መጠበቂያ ግንብ የመጨረሻ ገጽ ላይ ይወጣል። “የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው” የሚለውን ዓምድ የምንጠቀምበት መንገድ በአብዛኛው “ከአምላክ ቃል ተማር” ከሚለው ጋር ተመሳሳይ ነው። (km 12/10 ገጽ 2) ከዚህ ቀደም እንደነበረው ሁሉ የመንግሥት አገልግሎታችን በወሩ የመጀመሪያ ቅዳሜ የምንጠቀምበትን የአቀራረብ ናሙና ይዞ ይወጣል።