ሰዎች በመታሰቢያው በዓል ላይ እንዲገኙ የምንጋብዝበት ዘመቻ መጋቢት 22 ይጀምራል
ሰዎች በመታሰቢያው በዓል ላይ እንዲገኙ ለመጋበዝ የምናደርገው ዘመቻ በዚህ ዓመት ቅዳሜ፣ መጋቢት 22 ይጀምራል። ሁላችሁም የተሟላ ተሳትፎ እንድታደርጉ እናበረታታችኋለን። ቅዳሜና እሁድ ዘመቻውን ስናደርግ ሁኔታው አመቺ እንደሆነ ከተሰማን በቅርብ የወጡ መጽሔቶችንም ማበርከት እንችላለን። በሚያዝያ ወር የመጀመሪያ ቅዳሜ ላይ ትኩረት የምናደርገው ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዲጀምሩ በመጋበዝ ላይ ሳይሆን የመጋበዣ ወረቀቱን በማሰራጨት ላይ ነው። ይሁን እንጂ ከፍተኛ ፍላጎት ያለው ሰው ካገኘን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ልንጀምርለት እንችላለን። የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ፣ የመጋበዣ ወረቀቱን በአደባባይ ምሥክርነት አማካኝነት ማሰራጨት በክልሉ የሚገኙ ብዙ ሰዎችን ለማግኘት ይረዳ እንደሆነና እንዳልሆነ ይወስናል። ዘመዶቻችንን፣ የሥራ ባልደረቦቻችንን፣ አብረውን የሚማሩትንና ተመላልሶ መጠየቅ የምናደርግላቸውን ጨምሮ ሌሎች የምናውቃቸውን ሰዎች በሙሉ ለመጋበዝ ከአሁኑ የስም ዝርዝር ማውጣታችን ጠቃሚ ነው፤ ከዚያም ዘመቻው ሲጀምር የመጋበዣ ወረቀቱን ልንሰጣቸው እንችላለን። ይሖዋና ኢየሱስ ያሳዩንን ከሁሉ የላቀ ታላቅ ፍቅር ለማሰብ በምንሰበሰብበት ጊዜ ብዙዎች አብረውን እንደሚካፈሉ ተስፋ እናደርጋለን።—ዮሐ. 3:16፤ 15:13