የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 7/14 ገጽ 4
  • የአቀራረብ ናሙናዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአቀራረብ ናሙናዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2014
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በምታገኙት አጋጣሚ ሁሉ ተጠቀሙበት
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2010
  • የድረ ገጹን ትራክት ተጠቀሙ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2014
  • የአቀራረብ ናሙናዎች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2015
  • የአቀራረብ ናሙናዎች
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ (2016)
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2014
km 7/14 ገጽ 4

የአቀራረብ ናሙናዎች

በአእምሯችን ለሚጉላሉ ጥያቄዎች መልስ ማግኘት የሚቻለው ከየት ነው?

የቤቱ ባለቤት የትራክቱን ርዕስ እንዲመለከት አድርግ፤ ከዚያም እንዲህ በል፦ “ጤና ይስጥልን። በጣም አስፈላጊ መልእክት የያዘው ይህ ትራክት በዓለም ዙሪያ እየተሰራጨ ነው። ለእርስዎም ይህን ትራክት ብሰጥዎት ደስ ይለኛል።”

ቤት ውስጥ ሰው ከሌለ ትራክቱን አላፊ አግዳሚው እንዳያይ አድርገህ አስቀምጥ፤ የምታስቀምጠውን ትራክት ያለምክንያት ብዙ ቦታ አትጠፈው።

የቤቱ ባለቤት ፍላጎት ካሳየ ወይም መወያየት ከፈለገ በትራክቱ የፊት ገጽ ላይ ያለውን ጥያቄና የቀረቡትን አማራጭ መልሶች በማሳየት ሐሳብ እንዲሰጥ ጋብዘው። ትራክቱን ግለጥና መዝሙር 119:144, 160 ምን እንደሚል አሳየው። ትራክቱ፣ ሰዎች ለሚነሱባቸው ጥያቄዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ አጥጋቢ መልስ እንዲያገኙ ስለሚያስችላቸው አንድ ድረ ገጽ እንደሚናገር አብራራ። ምናልባትም መጽሐፍ ቅዱስን መማር የሚኖርብን ለምንድን ነው? የተባለውን ቪዲዮ እንደ ምሳሌ አድርገህ ልታሳየው ትችላለህ። ከመለያየታችሁ በፊት በትራክቱ የጀርባ ገጽ ላይ የሚገኙትን ሦስት ጥያቄዎች አሳየውና የበለጠ የሚያሳስበው የትኛው እንደሆነ ጠይቀው። ለመረጠው ጥያቄ መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን መልስ jw.org በተባለው ድረ ገጽ ላይ እንዴት ማግኘት እንደሚችል ለማሳየት ቀጠሮ ያዙ። በተመላልሶ መጠየቅ ወቅት የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች > የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው በሚለው ሥር በመመልከት የጥያቄውን መልስ አብራችሁ ተወያዩ።

በዚህ ዘመቻ ወቅት የክልል ስብሰባ መጋበዣ ወረቀት እያሰራጫችሁ ከሆነ የመጋበዣ ወረቀቱን ከትራክቱ ጋር አያይዘህ ለቤቱ ባለቤት ስጠው፤ ትራክቱን ስትሰጠው እንዲህ ልትለው ትችላለህ፦ “ይሄኛው ደግሞ በቅርቡ በምናደርገው ትልቅ ስብሰባ ላይ እንዲገኙ የሚጋብዝ የጥሪ ወረቀት ነው።”

መጠበቂያ ግንብ ነሐሴ 1

ቅዳሜና እሁድ አመቺ ከሆነ መጠበቂያ ግንብ ለማበርከት እንዲህ ማለት ትችላለህ፦ “በቅርብ ጊዜ የወጡ መጽሔቶችንም ብንሰጥዎት ደስ ይለናል። ይህ የመጠበቂያ ግንብ እትም ‘አምላክ ስለ አንተ ግድ ይሰጠዋል?’ ለሚለው ጥያቄ መልስ ይሰጣል።”

ንቁ! ነሐሴ

ቅዳሜና እሁድ አመቺ ከሆነ ንቁ! ለማበርከት እንዲህ ማለት ትችላለህ፦ “በቅርብ ጊዜ የወጡ መጽሔቶችንም ብንሰጥዎት ደስ ይለናል። ይህ የንቁ! እትም ‘ከሰዎች ጋር ሰላም መፍጠር የምንችለው እንዴት ነው?’ ለሚለው ጥያቄ መልስ ይሰጣል።”

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ