የአቀራረብ ናሙናዎች
መጠበቂያ ግንብ ሚያዝያ 1
“በዚህ አካባቢ ለምናገኛቸው ሰዎች ይህንን ትራክት እየሰጠናቸው ነው። [ለቤቱ ባለቤት ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ምን አመለካከት አለህ? የሚለውን ትራክት ስጠው፤ ከዚያም ፊተኛው ገጽ ላይ ያለውን ጥያቄ ጠይቀው። በመቀጠል መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን መልስ ከ2 ጢሞቴዎስ 3:16 ላይ አሳየው፤ እንዲሁም ጊዜ ሲያገኝ ትራክቱን እንዲያነበው አበረታታው።] ብዙ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ላሉ ጥያቄዎች መልስ እንደሚሰጥ አያውቁም። [በመጠበቂያ ግንቡ የመጀመሪያ ርዕስ መግቢያ ላይ የሚገኙትን ጥያቄዎች አሳየው።] ይህ መጽሔት መልሶቹን ከራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ማግኘት የሚችሉት እንዴት እንደሆነ ያብራራል።”
ንቁ! ሚያዝያ
“ብዙዎች በቤተሰብ ውስጥ ያለው ሁኔታ ከበፊቱ የተለየ መሆኑ ያሳስባቸዋል፤ ከሰዎች ጋር በዚህ ጉዳይ ላይ እየተነጋገርን ነበር። ድሮ ድሮ በቤተሰብ ውስጥ ሥልጣን ያላቸው ልጆች ሳይሆኑ ወላጆች ነበሩ፤ አሁን ግን ሁኔታው የተቀየረ ይመስላል። ለመሆኑ በዛሬው ጊዜ ያሉ ወላጆች፣ ልጆቻቸውን በመገሠጽ በሥርዓት እያሳደጓቸው እንደሆነ ይሰማዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ይህን ለማድረግ ተግሣጽ አስፈላጊ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። [ምሳሌ 29:17ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ልጆችን ከመገሠጽ ጋር በተያያዘ መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን ሚዛናዊ የሆነ ምክር ያብራራል።”