የአቀራረብ ናሙናዎች
መጠበቂያ ግንብ የካቲት 1
“በዚህ አካባቢ ለምናገኛቸው ሰዎች ይህንን ትራክት እየሰጠናቸው ነው። ትራክቱ መጽሐፍ ቅዱስ የሚጠቅመን እንዴት እንደሆነ ያብራራል። ይህን ያመጣሁት ለእርስዎ ነው። [ለቤቱ ባለቤት ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ምን አመለካከት አለህ? የሚለውን ትራክት ስጠው።] አንዳንድ ሰዎች ‘ከሥራዬ ጋር በተያያዘ ሊጠቅመኝ የሚችል ምክር ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ማግኘት እችላለሁ?’ ብለው ይጠይቃሉ። እዚህ ጥቅስ ላይ ሥራን በተመለከተ የተጠቀሰውን ሐሳብ ልብ ይበሉ። [መክብብ 3:13ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ከሥራችን ደስታ ማግኘት እንድንችል የሚረዱ አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎችን ይዟል። ወስደው እንዲያነቡት እጋብዝዎታለሁ።”
ንቁ! የካቲት
“በቅርቡ በወጣው ንቁ! መጽሔት ላይ ከጎረቤቶቻችን ጋር አጠር ያለ ውይይት እያደረግን ነበር። መጽሔቱ ትኩረት ለሚስብ አንድ ጥያቄ መልስ ይሰጣል። [የመጽሔቱን ሽፋን አሳየው።] በመጽሔቱ ላይ የተጠቀሰውን ይህን ምሳሌ በተመለከተ ምን ሐሳብ እንዳለዎት ቢነግሩኝ ደስ ይለኛል። [ምሳሌ 29:11ን አንብብ።] በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው ይህ ሐሳብ በዛሬው ጊዜም የሚጠቅም ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ይህ መጽሔት በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሚገኙ አራት መመሪያዎችን የሚጠቅስ ሲሆን እነዚህን መመሪያዎች ተግባራዊ ማድረጋችን የሚጠቅመን እንዴት እንደሆነም ያብራራል።”