አንዳችን ሌላውን ለመልካም ሥራ በቅንዓት እናነሳሳ
ዕብራውያን 10:24 ‘አንዳችን ሌላውን ለፍቅርና ለመልካም ሥራ እንድናነቃቃ’ ወይም እንድናነሳሳ ያበረታታናል። ምሳሌ በመሆንና እምነታችንን በተግባር በማሳየት ወንድሞቻችንን ማነሳሳት እንችላለን። ያገኛችኋቸውን አስደሳች ተሞክሮዎች በጉባኤ ውስጥ ላሉት ወንድሞችና እህቶች አካፍሉ። ይሖዋን ማገልገል ያስገኘላችሁን ደስታ እንዲመለከቱ አድርጉ። ይህን ስታደርጉ ግን እነሱን ከእናንተ ወይም ወይም ከሌሎች ጋር እንዳታወዳድሩ ተጠንቀቁ። (ገላ. 6:4) ያለንን ጠንካራ ጎን መጠቀም ያለብን ሌሎችን “ለፍቅርና ለመልካም ሥራዎች” ለማነሳሳት እንጂ የጥፋተኝነት ስሜት ተሰምቷቸው መልካም ነገር እንዲያደርጉ ለመጫን መሆን የለበትም። (የቲኦክራሲ መጽሐፍ ገጽ 158 አን. 4ን ተመልከት።) በመጀመሪያ ሌሎችን ለፍቅር ማነቃቃት ከቻልን እነሱ ራሳቸው መልካም ነገር ማድረጋቸው ማለትም ለሌሎች ቁሳዊ እርዳታ መስጠታቸው ወይም መስበካቸው አይቀርም።—2 ቆሮ. 1:24