በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—የመጽሔት ደንበኞች ማፍራት
አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? መጽሔቶቻችንን ማንበብ የሚያስደስታቸው ብዙ ሰዎች ከእኛ ጋር መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት አይፈልጉም። ይህ የሆነው ሃይማኖታቸውን መለወጥ ስለማይፈልጉ አሊያም ለማጥናት ጊዜ እንደሌላቸው ስለሚሰማቸው ይሆናል። ይሁንና መጽሔቶቻችንን አዘውትረው ማንበባቸው ለአምላክ ቃል ጉጉት እንዲያዳብሩ ሊያደርጋቸው ይችላል። (1 ጴጥ. 2:2) በመጽሔቶቻችን ላይ የወጣ ርዕስ ልባቸውን ሊነካው አሊያም ደግሞ ሁኔታቸው ሊለወጥ ይችላል። ከእነሱ ጋር በቋሚነት አጠር ያለ ውይይት የምናደርግ ከሆነ ከእኛ ጋር መወያየት ከባድ እንዳልሆነ ሊሰማቸው ይችላል፤ እኛም የሚፈልጓቸውንና የሚያሳስቧቸውን ነገሮች እንድናውቅ ይረዳናል። ውሎ አድሮ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት ሊጀምሩ ይችላሉ።
በዚህ ወር እንዲህ ለማድረግ ሞክሩ፦
የመጽሔት ደንበኛ ሊሆኑ የሚችሉ ሰዎችን ዝርዝር አዘጋጁ። በወሩ የወጡትን መጽሔቶች አበርክቱላቸው፤ እንዲሁም ቀጣዩን እትም እንደምታመጡላቸው ንገሯቸው።