ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | 2 ዜና መዋዕል 29-32
እውነተኛው አምልኮ ተግቶ መሥራት ይጠይቃል
በወረቀት የሚታተመው
ሕዝቅያስ ቆራጥ እርምጃ በመውሰድ እውነተኛውን አምልኮ መልሶ አቋቋመ
746-716 ዓ.ዓ.
የሕዝቅያስ የግዛት ዘመን
ኒሳን 746 ዓ.ዓ.
ቀን 1-8፦ የውስጠኛውን ግቢ አነጻ
ቀን 9-16፦ የይሖዋን ቤት አነጻ
የእስራኤላውያንን ኃጢአት የማስተሰረይና እውነተኛውን አምልኮ መልሶ የማቋቋም ሥራ ተጀመረ
740 ዓ.ዓ.
ሰማርያ ወደቀች
ሕዝቅያስ ቅን ልብ ያላቸው ሰዎች በሙሉ ለአምልኮ እንዲሰበሰቡ ጥሪ አስተላለፈ
ፋሲካ እንደሚከበር የሚገልጹ ደብዳቤዎችን ከቤርሳቤህ አንስቶ እስከ ዳን ድረስ በመላ ምድሪቱ እንዲያዳርሱ መልእክተኞች ተላኩ
አንዳንዶች ቢያፌዙም ብዙዎች ጥሩ ምላሽ ሰጥተዋል