ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | አስቴር 1–5
አስቴር ለአምላክ ሕዝቦች ጥብቅና ቆማለች
አስቴር የአምላክን ሕዝብ ለመታደግ የወሰደችው እርምጃ አስደናቂ እምነትና ድፍረት እንዳላት ያሳያል
ንጉሡ ፊት ሳይጠሩ መቅረብ ሞት ያስከትላል። አስቴር ደግሞ ለ30 ቀን ያህል ንጉሡ ወደ እሱ እንድትመጣ አልጋበዛትም ነበር
ንጉሥ አሐሽዌሮስ (ቀዳማዊ ጠረክሲስ እንደሆነ ይታሰባል) በቀላሉ የሚበሳጭ ሰው ነው። በአንድ ወቅት አንድ ሰው ሁለት ቦታ እንዲሰነጠቅና ለመቀጣጫነት ሌሎች እንዲያዩት ትእዛዝ አስተላልፎ ነበር። አስጢንም እሱን ለመታዘዝ ፈቃደኛ ባለመሆኗ ከንግሥናዋ ሽሯታል
አስቴር አይሁዳዊት መሆኗን መናገርና ንጉሡ የሚያምነው ሰው እንዳታለለው ማሳመን ይጠበቅባታል