የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb16 ሚያዝያ ገጽ 2
  • ውይይት ለመጀመር የሚረዳ አዲስ ዓምድ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ውይይት ለመጀመር የሚረዳ አዲስ ዓምድ
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ (2016)
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ይህን ዓምድ መጠቀም የሚቻልበት መንገድ፦
  • ስለ መንፈሳዊ ነገሮች መወያየት ያንጻል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2003
  • ትራክቶችን ተጠቅሞ ውይይት መጀመር
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2020
  • ጥያቄ በመጠየቅ፣ ጥቅስ በማንበብና አንድ ምዕራፍ አውጥቶ በማሳየት ጥናት ማስጀመር
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2006
  • አንድ ርዕሰ ጉዳይ ብቻ በማንሳት ሁለቱንም መጽሔቶች አበርክቱ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2013
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ (2016)
mwb16 ሚያዝያ ገጽ 2

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ውይይት ለመጀመር የሚረዳ አዲስ ዓምድ

በመቃብር ላይ ያለ ጽጌረዳ

ከጥር 2016 ጀምሮ ለሕዝብ የሚሰራጨው የመጠበቂያ ግንብ እትም “መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምራል?” የሚል ዓምድ በጀርባ ገጹ ላይ ይዞ ይወጣል። ይህ አዲስ ዓምድ የተዘጋጀው በመጽሐፍ ቅዱስ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ውይይት ለመጀመር እንድንጠቀምበት ነው። ይህ ዓምድ ከትራክቶቻችን ጋር ተመሳሳይ ገጽታ አለው። አንድ የአመለካከት ጥያቄና መጽሐፍ ቅዱስ ለዚያ ጥያቄ የሚሰጠውን መልስ እንዲሁም ለውይይት የሚሆኑ ተጨማሪ ሐሳቦችን ይዟል።

በመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳቦች ላይ የሚደረጉ ጥሩ ውይይቶች ብዙውን ጊዜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ይረዳሉ። ብዙ ሰዎች መንፈሳዊ ረሃባቸውን እንዲያስታግሱ ለመርዳት ይህን አዲስ ዝግጅት በሚገባ እንጠቀምበት።—ማቴ 5:6

ይህን ዓምድ መጠቀም የሚቻልበት መንገድ፦

  1. ከቀረቡት ጥያቄዎች መካከል አንዱን የቤቱን ባለቤት ጠይቅ

  2. አዳምጥ እንዲሁም ለሰጠው መልስ አመስግነው

  3. “መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?” ከሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር ያለውን ጥቅስ አንብብ፤ ከዚያም በጥቅሱ ላይ ሐሳብ እንዲሰጥ ጠይቅ። ግለሰቡ ጊዜ ካለው “መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ሌላስ ነገር አለ?” በሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር ያለውን ሐሳብ ተወያዩበት

  4. መጽሔቱን አበርክት

  5. ተመልሰህ በመምጣት በሁለተኛው ጥያቄ ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ያዝ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ