ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | መዝሙር 34-37
በይሖዋ ታመኑ፤ መልካም የሆነውንም አድርጉ
“በክፉ አድራጊዎች አትቅና”
ክፉዎች ያገኙት ጊዜያዊ ስኬት ይሖዋን ከማገልገል እንዲያደናቅፋችሁ አትፍቀዱ። በመንፈሳዊ በረከቶችና ግቦች ላይ ትኩረት አድርጉ
“በይሖዋ ታመን፤ መልካም የሆነውንም አድርግ”
ጭንቀት ላይ ስንወድቅ ወይም ደግሞ ጥርጣሬ ሲያድርብን ይሖዋ እንደሚረዳን መተማመን ይኖርብናል። ይሖዋ ምንጊዜም ታማኝ እንድንሆን ይረዳናል
የአምላክን መንግሥት ምሥራች በመስበኩ ሥራ ተጠመዱ
“በይሖዋ ሐሴት አድርግ”
የአምላክን ቃል የምታነቡበትና ባነበባችሁት ላይ የምታሰላስሉበት ጊዜ መድቡ፤ እንዲህ ስታደርጉ ዋናው ግባችሁ ይሖዋን ይበልጥ ማወቅ መሆን ይኖርበታል
“መንገድህን ለይሖዋ አደራ ስጥ”
ይሖዋ ማንኛውንም ችግር ለመወጣት እንደሚረዳችሁ ሙሉ እምነት ይኑራችሁ
ሰዎች ለእኛ የተሳሳተ አመለካከት በሚኖራቸው ወይም ተቃውሞና ስደት በሚያደርሱብን ጊዜም መልካም ምግባር ማሳየት ይኖርብናል
“በይሖዋ ፊት ዝም በል፤ እሱንም በተስፋ ተጠባበቅ”
ደስታችሁንና መንፈሳዊ ደኅንነታችሁን ሊያሳጣችሁ የሚችል የችኮላ እርምጃ ከመውሰድ ተቆጠቡ
“የዋሆች . . . ምድርን ይወርሳሉ”
የዋህነትን ፈልጉ፤ ይሖዋ የሚደርስባችሁን ግፍ እስኪያስወግደው ድረስ በትሕትና ጠብቁ
የእምነት ባልንጀሮቻችሁን ደግፉ፤ እንዲሁም አምላክ በቅርቡ አዲስ ዓለም እንደሚያመጣ የሰጠውን ተስፋ በመንገር የተጨነቁትን አጽናኑ
መሲሐዊው መንግሥት የተትረፈረፈ በረከት ያመጣል