የሚወደን ፈጣሪ ያዘጋጃቸውን ዘላለማዊ በረከቶች ማግኘት ትችላለህ
ጦርነት፣ ዓመፅና ሁከት በሌለበት ዓለም ውስጥ ለመኖር ትመኛለህ?
በሽታ፣ ሥቃይና ሞት ተወግደው ለማየት ትጓጓለህ?
ከጭንቀትና ከውጥረት የምትላቀቅበትን ጊዜ ትናፍቃለህ?
የተፈጥሮ አደጋዎች በሌሉበት አካባቢ መኖር ትፈልጋለህ?
ውብ የሆነችውን ምድራችንን የፈጠረው የሚወደን አምላካችን፣ ሰላምና ደስታ በሰፈነበት ዓለም ላይ ለዘላለም እንዲኖሩ በማድረግ የሰው ልጆችን እንደሚባርካቸው ቃል ገብቷል። ይህ ተስፋ የሕልም እንጀራ አይደለም።
በቀጣዮቹ ርዕሶች ላይ ለሚከተሉት ጥያቄዎች የተሰጠውን ማብራሪያ እንድታነብ እንጋብዝሃለን፦
ፈጣሪያችን ስለ ሰው ልጆች ምን ይሰማዋል?
በጽሑፍ የሰፈረው የአምላክ ቃል ለእኛ ምን መልእክት ይዟል?
የአምላክ ነቢያት እሱ ስለሰጣቸው ተስፋዎች ምን ተናግረዋል?
በአሁኑ ጊዜ ደስተኛ ሕይወት ለመምራት፣ ወደፊት አምላክ በወሰነው ጊዜ ደግሞ ዘላለማዊ በረከቶች ለማግኘት ምን ማድረግ ይጠበቅብናል?
እስቲ በመጀመሪያ ፈጣሪ ለሰው ልጆች ፍቅርና አሳቢነት እንዴት እንዳሳየ እንመልከት።