የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb16 ኅዳር ገጽ 3
  • መጽሐፍ ቅዱስ ባለሙያ ሚስትን የሚገልጽበት መንገድ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መጽሐፍ ቅዱስ ባለሙያ ሚስትን የሚገልጽበት መንገድ
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ (2016)
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አንዲት እናት የሰጠችው ጥበብ ያዘለ ምክር
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
  • ‘ባሏ በሰዎች ዘንድ በሰፊው የታወቀ ነው’
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ (2016)
  • ‘የሴት ራስ ወንድ ነው’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2021
  • ቤተሰብህ ደስተኛ ሊሆን የሚችለው እንዴት ነው?
    መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ (2016)
mwb16 ኅዳር ገጽ 3

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ምሳሌ 27-31

መጽሐፍ ቅዱስ ባለሙያ ሚስትን የሚገልጽበት መንገድ

ምሳሌ ምዕራፍ 31 የንጉሥ ልሙኤል እናት ለልጇ የተናገረችውን ከፍተኛ ቁም ነገር ያዘለ መልእክት ይዟል። የሰጠችው ጥበብ የሚንጸባረቅበት ምክር፣ አንዲት ባለሙያ ሚስት ተለይታ የምትታወቅባቸውን ነገሮች እንዲገነዘብ ረድቶታል።

ባለሙያ ሚስት እምነት የሚጣልባት ናት

በጥንት ዘመን የነበረች አንዲት ሴት ለቤተሰቧ ምግብ ስትሰጥ

31:10-12

  • ቤተሰቡን የሚመለከቱ ውሳኔዎች ሲኖሩ ለባሏ እንደምትገዛ በሚያሳይ መንገድ ጠቃሚ ሐሳብ ትሰጣለች

  • ባሏ ጥበብ የሚንጸባረቅባቸው ውሳኔዎች እንደምታደርግ ስለሚተማመንባት ለእያንዳንዱ ጉዳይ የእሱን ፈቃድ ማግኘት እንዳለባት አይሰማውም

ባለሙያ ሚስት ታታሪ ናት

በጥንት ዘመን የነበረች አንዲት ሴት እህል ስትፈጭ

31:13-27

  • የቤተሰቧ አባላት ንጹሕና ጥሩ አለባበስ እንዲኖራቸውና በደንብ እንዲመገቡ ለማድረግ ያላትን አብቃቅታ ለመጠቀም እንዲሁም በአቅሟ ለመኖር ትጥራለች

  • ቤተሰቧን ለመንከባከብ ቀን ከሌት ተግታ ትሠራለች

ባለሙያ ሚስት መንፈሳዊ ናት

አንዲት ሴት ስትጸልይ

31:30

  • አምላክን ትፈራለች፤ እንዲሁም ከእሱ ጋር የጠበቀ ዝምድና አላት

ይህን ታውቅ ነበር?

በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን ቀይ ዛጎል በጣም ተፈላጊ ነበር። ውብና በቀላሉ የማይገኝ ነገር ነበር። በሜድትራንያንና በቀይ ባሕር ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ሸቀጥ ነበር።

ቀይ ዛጎል

መጽሐፍ ቅዱስ ዛጎልን ከወርቅ፣ ከብርና ከሰንፔር ጋር አብሮ የሚጠቅሰው መሆኑ ዛጎል ትልቅ ዋጋ እንዳለው ያሳያል።

የአምላክ ቃል፣ ባለሙያ ሴት ‘ከዛጎል እጅግ እንደምትበልጥ’ ይናገራል።—ምሳሌ 31:10

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ