የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp20 ቁጥር 3 ገጽ 12
  • ለሌሎች ፍቅር ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ለሌሎች ፍቅር ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2020
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ቅዱሳን መጻሕፍት ስለ ፍቅር ምን ይላሉ?
  • ባልንጀራችንን መውደድ ሲባል ምን ማለት ነው?
  • “በፍቅር መመላለሳችሁን ቀጥሉ”
    ወደ ይሖዋ ቅረብ
  • ፍቅር (አጋፔ ) ምን አያደርግም? ምንስ ያደርጋል?
    መጠበቂያ ግንብ—1993
  • ፍቅር—ውድ የሆነ ባሕርይ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2017
  • እርስ በርስ ያለንን ፍቅር ማጠናከር የምንችለው እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2023
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2020
wp20 ቁጥር 3 ገጽ 12
ኢየሱስ በምሳሌው ላይ የጠቀሰው ሳምራዊ ሰው፣ ተደብድቦ መንገድ ዳር የተጣለውን ሰው ሲረዳው፤ ዘይት እያፈሰሰ ቁስሉን እያከመለት ነው።

ፍቅር ከራሳችን ይልቅ የሌሎችን ፍላጎት እንድናስቀድም ይገፋፋናል

ለሌሎች ፍቅር ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?

ሁላችንም የመጀመሪያው ሰው የአዳም ዘሮች በመሆናችን አንድ ቤተሰብ ነን ሊባል ይችላል። የአንድ ቤተሰብ አባላት ይዋደዳሉ እንዲሁም ይከባበራሉ፤ በዛሬው ጊዜ ግን እንዲህ ያለው ፍቅር ብርቅ ሆኗል። የሚወደን አምላካችን እንዲህ እንዲሆን አይፈልግም።

ቅዱሳን መጻሕፍት ስለ ፍቅር ምን ይላሉ?

“ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ።”—ዘሌዋውያን 19:18

“ጠላቶቻችሁን ውደዱ።”—ማቴዎስ 5:44

ባልንጀራችንን መውደድ ሲባል ምን ማለት ነው?

አምላክ ፍቅርን በተመለከተ በቃሉ ውስጥ ምን እንዳለ ለማወቅ እስቲ 1 ቆሮንቶስ 13:4-7⁠ን እንመልከት፦

“ፍቅር ታጋሽና ደግ ነው።”

እስቲ አስበው፦ በትዕግሥትና በደግነት ከሚይዙህ እንዲሁም በምትሳሳትበት ጊዜ ከማይቆጡህ ሰዎች ጋር ስትሆን ምን ይሰማሃል?

“ፍቅር አይቀናም።”

እስቲ አስበው፦ ሌሎች በጣም ሲጠራጠሩህ ወይም ሲመቀኙህ ምን ይሰማሃል?

ፍቅር “የራሱን ፍላጎት አያስቀድምም።”

እስቲ አስበው፦ አመለካከትህን ከሚያከብሩና ‘እኔ ያልኩት ካልሆነ’ ከማይሉ ሰዎች ጋር ስትሆን ምን ይሰማሃል?

“ፍቅር የበደል መዝገብ የለውም።”

እስቲ አስበው፦ አምላክ፣ የበደሉት ሰዎች በድርጊታቸው ሲጸጸቱ እነሱን ይቅር ለማለት ፈቃደኛ ነው። “እሱ ሁልጊዜ ስህተት አይፈላልግም፤ ለዘላለምም ቂም አይዝም።” (መዝሙር 103:9) ያስቀየምነው ሰው ይቅርታ ሲያደርግልን እንደሰታለን። እንግዲያው እኛም ሰዎች ሲያስቀይሙን ይቅር ለማለት ፈቃደኛ እንሁን።—መዝሙር 86:5

“ፍቅር በዓመፅ አይደሰትም።”

እስቲ አስበው፦ ሌሎች በደረሰብን መጥፎ ነገር ሲደሰቱ እናዝናለን። እኛም የበደሉን ሰዎች እንኳ ችግር ሲገጥማቸው ልንደሰት አይገባም።

የአምላክን በረከት ለማግኘት ለሁሉም ዓይነት ሰዎች በእነዚህ መንገዶች ፍቅር ማሳየት ይኖርብናል። ይህን ማድረግ የምንችልበት አንዱ መንገድ የተቸገሩትን መርዳት ነው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ