ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ኢሳይያስ 34-37
ሕዝቅያስ እምነት በማሳየቱ ተክሷል
የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም ኢየሩሳሌም እጇን እንድትሰጥ እንዲጠይቅ ራብሻቁን ወደ ኢየሩሳሌም ላከው። አሦራውያን፣ አይሁዳውያን ያለ ውጊያ እጃቸውን እንዲሰጡ ለማድረግ የተለያዩ ሐሳቦችን አቅርበዋል።
ረዳት እንደሌላቸው መናገር። ግብፅ ምንም ድጋፍ አትሰጣችሁም።—ኢሳ 36:6
ማስፈራራት። ኃያሉን የአሦር ሠራዊት መቋቋም አትችሉም። —ኢሳ 36:8, 9
ማባበያ። ለአሦር እጃችሁን ብትሰጡ የተሻለ ሕይወት መኖር ትችላላችሁ። —ኢሳ 36:16, 17
ሕዝቅያስ በይሖዋ ላይ የማይናወጥ እምነት ነበረው
ከተማይቱን ከወራሪዎች ለመታደግ አቅሙ የሚችለውን ሁሉ አድርጓል
ይሖዋ እንዲታደጋቸው ጸልዮአል፤ ሕዝቡም እንዲጸልዩ አበረታቷል
ይሖዋ አንድ መልአክ ልኮ 185,000 የአሦር ወታደሮችን በአንድ ሌሊት እንዲገድል በማድረግ ሕዝቅያስን ላሳየው እምነት ክሶታል