ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ኤርምያስ 17-21
ይሖዋ አስተሳሰብህንና ምግባርህን እንዲቀርጸው ፍቀድ
በይሖዋ ለመቀረጽ ፈቃደኛ ሁን
ይሖዋ ምክር ወይም ተግሣጽ በመስጠት መንፈሳዊ ባሕርያችንን ይቀርጽልናል
ታዛዦችና በቀላሉ የምንቀረጽ መሆን አለብን
ይሖዋ ያለፈቃዳችን ምንም ነገር እንድናደርግ አያስገድደንም
ሸክላ ሠሪው ሊሠራ ያሰበውን የሸክላ ዕቃ በተመለከተ ሐሳቡን ሊቀይርና ሌላ ዕቃ ሊሠራ ይችላል
ይሖዋ ነፃ ምርጫ ስለሰጠን በእሱ ለመቀረጽም ሆነ ላለመቀረጽ መምረጥ እንችላለን
ይሖዋ ሰዎች ለእሱ መመሪያ የሚሰጡትን ምላሽ ተመልክቶ እነሱን የሚይዝበትን መንገድ ይቀያይራል