የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb17 ሚያዝያ ገጽ 2
  • ሞቅ ያለ አቀባበል አድርጉላቸው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ሞቅ ያለ አቀባበል አድርጉላቸው
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2017
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በመታሰቢያው በዓል ላይ ጥሩ አቀባበል አድርጉላቸው
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
  • ትልቅ ምሥክርነት ይሰጣል
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2011
  • “ፍላጎት ያሳዩትን ሁሉ መርዳት
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
  • እንግዶቻችንን መቀበል
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ (2016)
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2017
mwb17 ሚያዝያ ገጽ 2

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ሞቅ ያለ አቀባበል አድርጉላቸው

ለእነማን? አዲሶችን እንዲሁም ለረጅም ጊዜ የምናውቃቸውን ጨምሮ በክርስቲያናዊ ስብሰባዎችን ላይ ለሚገኙ ሰዎች በሙሉ ሞቅ ያለ አቀባበል ማድረግ አለብን። (ሮም 15:7፤ ዕብ 13:2) በስብሰባዎቻችን ላይ ከሌላ አገር የመጡ የእምነት ባልንጀሮቻችን ወይም ከዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በስብሰባ ላይ የተገኙ የቀዘቀዙ ክርስቲያኖች ይገኙ ይሆናል። እናንተ እንዲህ ባለው ሁኔታ ሥር ብትሆኑ ምን ሊሰማችሁ እንደሚችል ለማሰብ ሞክሩ። ሞቅ ያለ አቀባበል ቢደረግላችሁ ደስ አይላችሁም? (ማቴ 7:12) ታዲያ ስብሰባው ከመጀመሩ በፊትና ካለቀ በኋላ በመንግሥት አዳራሹ ውስጥ ተዘዋውራችሁ ሌሎችን ሰላም ለማለት ለምን ጥረት አታደርጉም? እንዲህ ማድረጋችሁ በስብሰባዎቻችን ላይ ሞቅ ያለ መንፈስና ፍቅር እንዲሰፍን አስተዋጽኦ ያደርጋል፤ እንዲሁም ይሖዋን ያስከብረዋል። (ማቴ 5:16) እርግጥ ነው፣ በስብሰባው ላይ የተገኘውን እያንዳንዱን ሰው ማነጋገር አይቻል ይሆናል። ሆኖም ሁላችንም የበኩላችንን ጥረት ካደረግን በስብሰባው ላይ የተገኘ ማንኛውም ሰው የእንግድነት ስሜት አይሰማውም።a

እንግዳ ተቀባይ መሆን ያለብን እንደ መታሰቢያው በዓል ባሉ ለየት ያሉ ዝግጅቶች ላይ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ጊዜያት ነው። አዲሶች፣ ክርስቲያናዊ ፍቅር በተግባር ሲገለጽ ሲያዩና እነሱም እንዲህ ያለውን ፍቅር ሲያጣጥሙ አምላክን ለማወደስና ከእኛ ጋር አብረው በእውነተኛው አምልኮ ለመካፈል ሊነሳሱ ይችላሉ።—ዮሐ 13:35

a የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች በስብሰባ ላይ የሚገኙ ከጉባኤ የተወገዱ ወይም ራሳቸውን ያገለሉ ሰዎችን ሰላም ማለት እንደሌለብን በግልጽ ያሳያሉ።—1ቆሮ 5:11፤ 2ዮሐ 10

አንድ ወንድም ወደ ጉባኤ የመጡ አዳዲስ ሰዎችን በደስታ ሲቀበላቸው

አዲሶችን መርዳት የምንችለው እንዴት ነው?

  • ራሳችንን ማስተዋወቅ እንዲሁም ስማቸውን መጠየቅ

  • አብረውን እንዲቀመጡ መጋበዝ

  • መጽሐፍ ቅዱስና የመዝሙር መጽሐፍ አብረውን እንዲከታተሉ ማድረግ

  • ከስብሰባው በኋላ ጥያቄ ካላቸው ጥያቄያቸውን ለመመለስ ፈቃደኛ እንደሆንን መግለጽ

  • እንደ ሁኔታው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዲጀምሩ ግብዣ ማቅረብ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ