ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ኤርምያስ 25-28
ልክ እንደ ኤርምያስ ደፋሮች ሁኑ
ኤርምያስ ኢየሩሳሌም ልክ እንደ ሴሎ ድምጥማጧ እንደሚጠፋ ተናግሯል
የይሖዋን መገኘት የሚያመለክተው የቃል ኪዳኑ ታቦት በሴሎ ይቀመጥ ነበር
ይሖዋ ፍልስጤማውያን ታቦቱን ማርከው እንዲወስዱ የፈቀደ ሲሆን ታቦቱም ዳግመኛ ወደ ሴሎ አልተመለሰም
ካህናቱ፣ ነቢያቱና ሕዝቡ ኤርምያስን እንደሚገድሉት ዝተውበት ነበር
ኤርምያስ ኢየሩሳሌምንና ቤተ መቅደሱን በተመለከተ የጥፋት መልእክት በማወጁ ምክንያት ሕዝቡ ያዘው
ኤርምያስ በሁኔታው ተስፋ ቆርጦ ወደኋላ አላለም
ይሖዋ ኤርምያስን ጠብቆታል
ኤርምያስ እስከ መጨረሻው ደፋር መሆኑን አሳይቷል፤ ይሖዋም አልተወውም
አምላክ ደፋር በሆነው አኪቃም አማካኝነት ኤርምያስን ከጉዳት ጠብቆታል
ኤርምያስ የሚያውጀው መልእክት ሕዝቡን የሚያበሳጭ ቢሆንም በይሖዋ ድጋፍና ማበረታቻ ለ40 ዓመታት ያህል ይህን መልእክት ማወጁን ሊቀጥል ችሏል