የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb17 ሚያዝያ ገጽ 6
  • የመንግሥቱ መዝሙሮች ድፍረት ይሰጣሉ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመንግሥቱ መዝሙሮች ድፍረት ይሰጣሉ
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2017
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ለይሖዋ የውዳሴ መዝሙር በደስታ ዘምሩ
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2018
  • ለጥናት የሚረዱ ሐሳቦች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2023
  • ለአምልኮ የምንጠቀምባቸው አዳዲስ መዝሙሮች!
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2014
  • በስብሰባዎቻችን ላይ ለይሖዋ ለመዘመር ተዘጋጅታችኋል?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2009
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2017
mwb17 ሚያዝያ ገጽ 6

ክርስቲያናዊ ሕይወት

የመንግሥቱ መዝሙሮች ድፍረት ይሰጣሉ

ወንድም ኤሪክ ፍሮስት ፒያኖ አጠገብ ተቀምጦ

ጳውሎስና ሲላስ እስር ቤት በነበሩበት ወቅት አምላክን በመዝሙር አወድሰዋል። (ሥራ 16:25) በዘመናችንም ቢሆን በናዚ ጀርመን በዛክሰንሃውዘን ማጎሪያ ካምፕና በሳይቤሪያ በግዞት የነበሩ ወንድሞቻችን የመንግሥቱን መዝሙሮች ይዘምሩ ነበር። ከእነዚህ ምሳሌዎች ማየት እንደሚቻለው መዝሙሮች ፈተና እየደረሰባቸው ላሉ ክርስቲያኖች ድፍረት የመስጠት ኃይል አላቸው።

ለይሖዋ ‘በደስታ ዘምሩ’ የተባለው አዲስ የመዝሙር መጽሐፍ በቅርቡ በበርካታ ቋንቋዎች ይዘጋጃል። መጽሐፉ እንደደረሰን መዝሙሮቹን በቤተሰብ አምልኮ ፕሮግራማችን ላይ በመለማመድ ግጥሞቹን በቃላችን ለመያዝ ጥረት እናድርግ። (ኤፌ 5:19) እንዲህ ካደረግን በፈተና ውስጥ በምንሆንበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ መዝሙሮቹን እንድናስታውስ ይረዳናል። የመንግሥቱ መዝሙሮች በተስፋችን ላይ ትኩረት እንድናደርግ ይረዱናል። በፈተና ውስጥ ስንሆን ያደፋፍሩናል። ጥሩ ስሜት ሲሰማን ደግሞ የሚያነቃቁ ግጥሞች ያሏቸው መዝሙሮቻችን የልባችንን ሐሴት እንድንገልጽና ‘በደስታ እንድንዘምር’ ያስችሉናል። (1ዜና 15:16፤ መዝ 33:1-3) እንግዲያው ሁላችንም ከመንግሥቱ መዝሙሮች ጥቅም ለማግኘት የቻልነውን ያህል ጥረት እናድርግ!

የጉልበት ሠራተኞችን ያበረታታ መዝሙር የሚለውን ቪዲዮ ተመልከቱ። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክሩ፦

  • ወንድም ፍሮስት መዝሙር እንዲያቀናብር ያነሳሳው ምንድን ነው?

  • መዝሙሩ በዛክሰንሃውዘን ማጎሪያ ካምፕ ውስጥ የነበሩ ወንድሞችን ያበረታታቸው እንዴት ነበር?

  • በዕለት ተዕለት በሚያጋጥሙህ በየትኞቹ ሁኔታዎች ሥር የመንግሥቱ መዝሙሮች ሊያጠናክሩህ ይችላሉ?

  • ከመንግሥቱ መዝሙሮች መካከል የትኞቹን በቃልህ መያዝ ትፈልጋለህ?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ