ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ኤርምያስ 35-38
ኤቤድሜሌክ—ድፍረትና ደግነት በማሳየት ረገድ ግሩም ምሳሌ ትቷል
በንጉሥ ሴዴቅያስ ቤተ መንግሥት የነበረ ኤቤድሜሌክ የተባለ መኮንን አምላካዊ ባሕርያት አሳይቷል
ኤርምያስን በተመለከተ ንጉሥ ሴዴቅያስን በማነጋገር እንዲሁም ኤርምያስን ከጉድጓዱ በማውጣት በድፍረት ፈጣን እርምጃ ወስዷል
ገመዱ ብብቱን እንዳይጎዳው የተቦጫጨቀ ጨርቅና ልብስ ለኤርምያስ በመስጠት ደግነት አሳይቷል