ክርስቲያናዊ ሕይወት
ይሖዋ ያሳያችሁትን ፍቅር አይረሳም
ይሖዋ ያሳያችሁትን ፍቅር አይረሳም የተባለውን ቪዲዮ ከተመለከታችሁ በኋላ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክሩ፦
የዕድሜ መግፋት ምን ተፈታታኝ ሁኔታዎችን ያስከትላል?
በዕድሜ የገፉ አብዛኞቹ ሰዎች የትኛው ጥሩ ባሕርይ ይኖራቸዋል?
በዕድሜ የገፋህ ከሆንክ ዘሌዋውያን 19:32 እና ምሳሌ 16:31 ላይ የሚገኘው ሐሳብ የሚያበረታታህ እንዴት ነው?
ይሖዋ በዕድሜ በመግፋታቸው ምክንያት የቀድሞውን ያህል ማገልገል ያልቻሉትን አገልጋዮቹን እንዴት ይመለከታቸዋል?
ይሖዋ ዕድሜያችን ከገፋ በኋላም ምን እንድናደርግ ይፈልግብናል?
በዕድሜ የገፉ ክርስቲያኖች ወጣቶችን ማበረታታት የሚችሉት እንዴት ነው?
በዕድሜ የገፉ አንድ ወንድም ወይም እህት በቅርቡ ያበረታቱህ እንዴት ነው?