ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ኤርምያስ 44-48
“ለራስህ ታላላቅ ነገሮችን” አትፈልግ
ባሮክ የተማረና በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ሥልጣን የነበረው ሰው ሳይሆን አይቀርም። ይሖዋን ያመልክና ኤርምያስን በታማኝነት ይረዳ የነበረ ቢሆንም በአንድ ወቅት ሚዛኑን ስቶ ነበር። ለራሱ “ታላላቅ ነገሮችን” መፈለግ ጀምሮ ነበር፤ ምናልባትም በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ተጨማሪ ሥልጣን ማግኘት ወይም ተጨማሪ ቁሳዊ ሀብት ማካበት ፈልጎ ሊሆን ይችላል። እየተቃረበ ከነበረው የኢየሩሳሌም ጥፋት ለመትረፍ አስተሳሰቡን ማስተካከል ያስፈልገው ነበር።