ክርስቲያናዊ ሕይወት
አምላክን የሚያስደስቱ ባሕርያትን አዳብሩ—ድፍረት
አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
ምሥራቹን መስበክ ድፍረት ይጠይቃል።—ሥራ 5:27-29, 41, 42
በታላቁ መከራ ወቅት ድፍረት የሚጠይቁ ነገሮች ያጋጥሙናል።—ማቴ 24:15-21
ሰውን መፍራት አሳዛኝ መዘዝ ያስከትላል።—ኤር 38:17-20፤ 39:4-7
ይህን ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?
ከአገልግሎት ጋር በተያያዘ የሚያስፈራኝ ነገር ምንድን ነው? እንዴትስ ልቋቋመው እችላለሁ?
ታማኝነትን የሚሸረሽሩ ነገሮችን አስወግዱ—ሰውን መፍራት የተባለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
አገልግሎታችንን ለማከናወን ድፍረት የግድ አስፈላጊ ነው የምንለው ለምንድን ነው?
ምሳሌ 29:25 ላይ የትኞቹ ነገሮች በንጽጽር ቀርበዋል?
አሁኑኑ ድፍረት ማዳበር ያለብን ለምንድን ነው?