ክርስቲያናዊ ሕይወት
አምላክን የሚያስደስቱ ባሕርያትን አዳብሩ—እምነት
አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
አምላክን በሚገባ ደስ ለማሰኘት እምነት ያስፈልጋል።—ዕብ 11:6
አምላክ በሰጠን ተስፋዎች ላይ እምነት ማሳደራችን ፈተናዎችን በጽናት ለመወጣት ይረዳናል።—1ጴጥ 1:6, 7
እምነት ማጣት ኃጢአት ወደመፈጸም ሊመራ ይችላል።—ዕብ 3:12, 13
ይህን ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?
እምነት ካላቸው ሰዎች ጋር አዘውትረህ ተሰብሰብ።—ሮም 1:11, 12
የራሴንም ሆነ የቤተሰቦቼን እምነት ማጠናከር የምችለው እንዴት ነው?
ታማኝ ለመሆን የሚረዱ ባሕርያትን አዳብሩ—እምነት የተባለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦