ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ሕዝቅኤል 42-45
ንጹሑ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
ሕዝቅኤል በራእይ ቤተ መቅደሱን ማየቱ፣ በምርኮ ላሉት ታማኝ አይሁዳውያን ቀሪዎች ንጹሑ አምልኮ መልሶ እንደሚቋቋም ማረጋገጫ ሆኗቸዋል። በተጨማሪም ይሖዋ ለንጹሕ አምልኮ ላቅ ያለ መሥፈርት እንዳለው አስታውሷቸዋል።
• ካህናቱ የይሖዋን መሥፈርቶች ለሕዝቡ ያስተምራሉ
ታማኝና ልባም ባሪያ፣ ንጹሕ ባልሆነውና ንጹሕ በሆነው ነገር መካከል ያለውን ልዩነት ያስተማረን እንዴት እንደሆነ የሚያሳዩ አንዳንድ ምሳሌዎችን ጥቀስ። (kr 110-117)
• ሕዝቡ አመራር የሚሰጡ ሰዎችን ይደግፋል
በጉባኤ ውስጥ ያሉትን ሽማግሌዎች እንደምንደግፍ ማሳየት የምንችልባቸው አንዳንድ መንገዶች የትኞቹ ናቸው?