ከመስከረም 4-10
ሕዝቅኤል 42-45
መዝሙር 31 እና ጸሎት
የመግቢያ ሐሳብ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
“ንጹሑ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!”፦ (10 ደቂቃ)
ሕዝ 43:10-12—ይሖዋ፣ ሕዝቅኤል ስለ ቤተ መቅደሱ ራእይ እንዲያይ አድርጓል፤ ይህን ያደረገው በምርኮ ያሉት አይሁዳውያን ንስሐ ለመግባት እንዲነሳሱ ሊረዳቸው እንዲሁም ንጹሑ አምልኮ ወደ ቀድሞው ላቅ ያለ ቦታው እንደሚመለስ ሊያረጋግጥላቸው ስለፈለገ ነው (w99 3/1 8 አን. 3፤ it-2-E 1082 አን. 2)
ሕዝ 44:23—ካህናቱ ‘ንጹሕ ባልሆነውና ንጹሕ በሆነው ነገር መካከል ያለውን ልዩነት’ ለሕዝቡ ያስተምሯቸዋል
ሕዝ 45:16—ሕዝቡ፣ ይሖዋ አመራር እንዲሰጡ የሾማቸውን ሰዎች ይደግፋል (w99 3/1 10 አን. 10)
መንፈሳዊ ዕንቁዎችን በምርምር ማግኘት፦ (8 ደቂቃ)
ሕዝ 43:8, 9—እስራኤላውያን የአምላክን ስም ያረከሱት በምን መንገድ ነው? (it-2-E 467 አን. 4)
ሕዝ 45:9, 10—ይሖዋ፣ ሞገሱን ማግኘት የሚፈልጉ ሰዎች ሁሉ ምን እንዲያደርጉ ይጠብቅባቸዋል? (it-2-E 140)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ስለ ይሖዋ ምን ትምህርት አግኝታችኋል?
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን ሌሎች መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) ሕዝ 44:1-9
በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር
የዚህን ወር መግቢያዎች መዘጋጀት፦ (15 ደቂቃ) “የመግቢያ ናሙናዎች” በሚለው ርዕስ ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። እያንዳንዱን የመግቢያ ናሙና ቪዲዮ አጫውት፤ ከዚያም ጎላ ባሉ ነጥቦች ላይ ተወያዩ።
ክርስቲያናዊ ሕይወት
“ንጹሑን አምልኮ ከፍ አድርገህ የምትመለከተው ለምንድን ነው?”፦ (15 ደቂቃ) በውይይት የሚቀርብ።
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (30 ደቂቃ) kr ምዕ. 14 አን. 15-23 እና “የአምላክ መንግሥት ለአንተ ምን ያህል እውን ነው?” የሚለው የክለሳ ሣጥን
ክለሳና የቀጣዩ ሳምንት ማስተዋወቂያ (3 ደቂቃ)
መዝሙር 97 እና ጸሎት