መዝሙር 77
በጨለማ ዓለም ውስጥ ብርሃን ማብራት
በወረቀት የሚታተመው
1. እነዚህ ጨለማ ቀናት
ባመፅ ተሞልተዋል።
ይታያል የተስፋ ብርሃን፤
በቅርቡ ይነጋል።
(አዝማች)
መል’ክታችን ብሩህ፣
በጨለማ ያበራል፤
ተስፋ፣ ብርሃን ይዟል።
እንደ ንጋት ጸዳል፣
ከጨለማው ባሻገር
ያሳየናል።
2. የተኙ ከ’ንቅልፍ ይነሱ፤
አልቋልና ጊዜው።
በተስፋው እናጽናናቸው፤
እንጸልይላቸው።
(አዝማች)
መል’ክታችን ብሩህ፣
በጨለማ ያበራል፤
ተስፋ፣ ብርሃን ይዟል።
እንደ ንጋት ጸዳል፣
ከጨለማው ባሻገር
ያሳየናል።
(በተጨማሪም ዮሐ. 3:19፤ 8:12ን፣ ሮም 13:11, 12ን እና 1 ጴጥ. 2:9ን ተመልከት።)