ክርስቲያናዊ ሕይወት
ይሖዋን ሁልጊዜ እንዲያገለግሉ አሠልጥኗቸው
አዳዲስ አስፋፊዎች ከመጀመሪያው አንስቶ በአገልግሎት አዘውትረው በቅንዓት እንዲካፈሉ ሥልጠና ከተሰጣቸው ውጤታማ አስፋፊዎች እንደሚሆኑ ተሞክሮዎች ያሳያሉ። (ምሳሌ 22:6፤ ፊልጵ 3:16) ጥናትህ በአገልግሎት ረገድ ጥሩ መሠረት እንዲኖረው መርዳት የምትችልባቸው አንዳንድ መንገዶች ከዚህ በታች ቀርበዋል፦
ጥናትህ አስፋፊ እንዲሆን ከተፈቀደለት ጊዜ አንስቶ ማሠልጠን ጀምር። (km 8/15 1) በሳምንታዊ ፕሮግራሙ ውስጥ አገልግሎትን ማካተቱ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ አበክረህ ግለጽ። (ፊልጵ 1:10) ስለ አገልግሎት ክልላችሁ በምትናገርበት ወቅት አዎንታዊ ሁን። (ፊልጵ 4:8) ሌሎች ካላቸው ተሞክሮ ትምህርት ማግኘት እንዲችል ከቡድን የበላይ ተመልካቹና ከሌሎች አስፋፊዎች ጋር እንዲያገለግል አበረታታው።—ምሳሌ 1:5፤ km 10/12 6 አን. 3
ጥናትህ ከተጠመቀ በኋላም እሱን ማበረታታትህንና ለአገልግሎት ማሠልጠንህን አታቋርጥ፤ በተለይ “ከአምላክ ፍቅር” የተባለውን መጽሐፍ አጥንቶ ካልጨረሰ ይህን ማድረግህ አስፈላጊ ነው። —km 12/13 7
ከአዲስ አስፋፊ ጋር በምታገለግልበት ወቅት ቀላል መግቢያ ተጠቀም። አስፋፊው አንድን ሰው ካናገረ በኋላ በደንብ አመስግነው። እንዲሁም ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን የሚረዱትን አንዳንድ ሐሳቦች አካፍለው።—km 5/10 7